የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ምሥጋናና መልእክት

መ/ሕ ቆሞስ አባ ኃ/ገብርኤል ነጋሽ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መግለጫ ሲሰጡ።

በዛሬው የነግህ የጸሎተ-ዕጣንና የማዕጠንት አገልግሎት ለተሳተፋችሁ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ካህናት በሀገረ ስብከታችን ጽ/ቤት ስም ምሥጋናችንን እናቀርባለን፡፡
የአቀረብነውን የዕጣን መሥዋዕት እንዲሰምርልንና ይህንን በሽታ ከሀገራችንና ከመላው ዓለም እንዲያስወግድልን ኦርቶዶክሳውያን ሁላችን ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጀውን የጸሎትና የምህላ ጥሪ በመቀበል በየአጥቢያችን ተሳትፎ እንድናደርግ እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች የሚነግሩንን ሙያዊ ምክሮች የመተግበር ግዴታ እንዳለብን መዘንጋት የለብንም፡፡
እግዚአብሔር አገራችንና መላውን ዓለም ከመቅሰፍት ይሰውርልን፡፡
መ/ሕ ቆሞስ አባ ኃ/ገብርኤል ነጋሽ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ