የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ‹‹ እልልታ ውመንአትሪስክ ›› ከተበለ ሀገር በቀል በጎ አድራጊ ድርጅት ጋር በመተባበር የሴተኛ አዳሪነትን ሥራ ለማስቆም ለአድባራት እና ገዳማት ተወካዮች የአንድ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ
ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሀገረ ስብከቱ ምግባረ ሠናይ ዋና ክፍል በቀረበው ጥናት መሠረት እልልታውመን አትሪስክ ከተባለ አንድ ሀገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር ቁጥራቸው ሰባ ለሚደርሱና ለተመረጡ የአድባራት አስተዳዳሪዎች እና ሰባክያነ ወንጌል ቅዳሜ መስከረም 24 ቀን 2007 ዓ.ም አስከፊ የሆነውን የሴተኛ አዳሪነት (የዝሙት) ሥራ ለማስቆም የሚአስችል የአንድ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሰጠ ሲሆን የድርጅቱ መሥራች ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሠራዊት ተከተል በሥልጠናው መጀመሪያ ላይ ባደረጉት ምሳሌአዊ እና ፈሊጣዊ የመክፈቻ ንግግር የሴተኛ አዳሪነት ሕይወት እጅግ የከፈና አጸያፊ ሲሆን በፈጣሪም ዘንድ በኃጢአተኝነት የሚአስቀጣ ነው፡፡
ይህ የነውር ተግባር በርካታ ሴቶች እህቶቻቸንን ለከፋ ሕይወት እየዳረጋቸው የሚገኝ መሆኑን ድርጅታችን የተገነዘበው በመሆኑ ለረጅም ዓመታት አቅሙ የፈቀደለትን ያህል ሲሠራ ቆይቷል፡፡ አንድ ምሳሌ መጥቀስ ቢቻል ባንድ ወቅት በባህር ዳር አካባቢ በሚገኘው ደሴት ውስጥ የሚኖሩ አሳዎች ማዕበሉ እየገፈተረ ከባህሩ ወደ የብስ በብዛት መውጣታቸውን የተመለከተ አንድ ግለሰብ ያልሞቱትን አሳዎች ከእልቂት ለመታደግ እያንዳንዱን አሳ በእጁ እያነሳ ወደ ባህሩ እየወረወረ ሲጨምራቸው የተመለከተ ሌላ ሰው ወዳጄ ሆይ በየቀኑ የሚሞተው አሳ ብዙ ነው አሁን ይህንን ሁሉ አሳ ለመታገድ ብለህ ነውን የምታደክመው ብሎ ቢጠይቀው ግለሰቡ አንዷን አሳ በእጁ አንስቶ ያዘና ለዚህች ለአንዲቱ አሳ ለሚተርፈው ሕይወት ብዙ ትርጉም አለው በማለት መልስ ሰጣቸው ይባላል፡፡
የእሎልታውመን አትሪስክ ሥረም ከብዙ የሚጠፋ የሰው ሕይወት አንዱ እንኳን ሕይወት ማትረፉ ትርጉም አለው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከመቶ ሀምሳ ሺህ በላይ የዝሙት አዳሪ ሴቶች እንደሚኖሩ የድርጅቱ ጥናት አረጋግጧል፡፡ እነዚህ ሴቶች እህቶቻችን በተሠማሩበት የዝሙት ሥራ ገንዘብ ለማግኘት በቀን ከሰባት ከማያንሱ ወንዶች ጋር በዝሙት ይወድቃሉ፡፡
ስለዚህ የችግሩ አሳሳቢነት እየገፉ በመምጣቱ የሴተኛ አዳሪዎችም ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ በሃይማኖት አባቶች በኩል ትምህርቱ ቢሰጥ ችግሩ ሊፈታ ይቻላል በሚል እምነት ‹‹ እልልታውመን አትሪስክ ›› የበጎ አድራጎት ድርጅት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናውን ከሀገረ ስብከቱ ጋር በመተባበር ሊአከናውን ችሎአል በማለት ሥራ አስኪያጅዋ ሰፋ ያለ ማብራርያ ሰጥተዋል ፡፡
በመቀጠልም የሀገረ ስብከቱ ወኪል ሆነው በስልጠናው ላይ የተገኙት ንቡረ ዕድ አባ ዮሐንስ ገብረ ሕይወት ራስህን ላክህን አሳይ በሚል መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ ጀምረው ይህን አስከፊና አጸያፊ ተግባር ለመከላከል ቤተ ክርስቲያናችን የማስተማር ግዴራ አለባት ዋና ተልዕኮዋም ይህ ነው ‹‹ እልልታውመን አትሪስክ ›› ከሀገረ ስብከታችን ጋር በመተባበር ይህንን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በማዘጋጀቱ ሊመሰገን ይገባል፡፡ እኛም በዚህ የስልጠና ውይይት ጥሩ ግንዛቤ በመውሰድ ኃላፊነታችንን ተግተን ልንወጣ ይገባናል በማለት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ከዚያም በአንድ ባለሙያ የሴተኛ አዳሪነት ሕይወር ሃይማኖታዊ እና ማህበራዊ ተግዳሮቱ በሚል ርዕስ የዝሙት ተግባርን ሥራ የመከላከል ዋና ኃላፊነት የቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ወደ ሰባክያነ ወንጌል ወደ አበ ነፍሶች ( የንስሐ አባት ) መሄድ አለበት ያን ጊዜ ነው የሴተኛ አዳሪነትን ሕይወት ማስቆም የሚቻለው ፡፡
በትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 8፡-21 ላይ ስንመለከት ‹‹ በሕዝቤ ሴት ልጅ ስብራት እኔ ተሰብሬአለሁ ›› ጠቁሬማለሁ አድናቆትም ይዞኛል በገለአድ የሚቀባ መድኃኒት የለምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለምን? የወገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለምን አልሆነም? ‹‹ ተወግተው ስለሞቱ ስል ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊት እና ቀን አለቅስ ዘንድ ራሴ ውኃ አይኔም የእንባ ምንጭ በሆነ (ኤር 9፡-1)
በዓለማችን የሴተኛ አዳሪነት ሕይወት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶአል፡፡ ከሰዎች ሕገ ወጥ ዝውውር ጋር ተያያዥነት አለው፡፡
ፈረንሳይ፣አሜሪካ፣ኮሎምቢያ እና በመሳሰሉት ሀገሮች ችግሩ ዓለም አቀፍ ነው፡፡ በዚህ በሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሰው ልጅ እንደ እንስሳ የሚሸጥበት ዘመን ነው፡፡ በአፍሪካም ከእንድስትሪ አብዮት ጋር ተያይዞ ይህ የዝሙት ሕይወት እያደገ ነው የመጣው በአፍሪካም ከቅኝ ግዛትም ጋር ተያይዞ እንደተጀመረ ይነገራል፡፡
ስለዚህ የሴተኛ አዳሪነት ሕይወት በሁሉም የአፍሪካ ሀገሮች በከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶአል፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያም ስንመለከት ከግራኝ መሀመድ ወረራ ጋር ተያይዞ በተለይ ሁለት፣ሶስት፣አራት ሴት የማግባቱ ጉዳይ ከዚያው ባህል ጋር ተያይዞ የመጣው ችግር መነሻ መሆኑን መዛግብቶች ይናገራሉ፡፡ በተለይም ከጣሊያን ወረራ ጋር ተያይዞ መሸታ ቤቶች፣የጭፈራ ቤቶች እየተከፈቱ ሲሄዱ የቀኝ ገዢው የጣሊያን ሠራዊቶች በሴቶች ላይ የፈጠሩት አፀያፊ ተግባር በዋናነት ይጠቀሳል፡፡ ይህ ችግር ከዚያ ተነስቶ ነው አሁን አለበት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰው የሴተኛ አዳሪነት ሕይወት በሀገርም ላይ ሆነ በቤተክርስቲያን ላይ ጫና ሊአሰድር እንደሚችሉም ጭምር በመረጃ የተደገፈ ትምህርታዊ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በማያያዝም ሌላው ባለሙያ አስከፊውን የዝሙት ሕይወት አስመልክቶ የተቀረፀውን የቪድዎ መረጃ በእስክሪንና በፕሮጀክተር በተደገፈ ስዕላዊ መረጃ በማቅረብ የጉዳዩን ዘግናኝነት እና አፀያፊነት በዚሁ በሴተኛ አዳሪነት (ዝሙት) ሥራ የተሠማሩት ሴቶች ሕይወታቸው ከምን ላይ እንዳለ በየዕለቱ የሚደርስባቸውን ጉዳት ወደዚህ ሕይወት የገቡበትን ምክንያት የተናገሩትን ለተሳታፊዎች በምስል የተደገፈ መረጃ ቀርቦአል፡፡ እልልታውመን አትሪስክ ያማከራቸው 654 የሴቶች እህቶቻችንን የትምህርት ወ ዘ ተ ታሪክ የያዘ በግራፍ መልክ የተዘጋጀ ዳታና አሀዛዊ መረጃም ቀርቧል፡፡ ከዚያም በኋላ የስልጠናው ተሳታፊዎች በሶስት ቡድን በመደራጀት የቡድን ውይይት በማድረግ የችግሩን መነሻና የመፍትሔ አቅጣጫ በመጠቆም የዕለቱ የስልጠና መርሐ ግብር ተጠናቋል፡፡
በመጨረሻም ከስብክተ ወነጌል አገልጊሎት ዋናውና ተቀዳሚው የቤተ ክርስቲያን ዓላማ ይህንን በጎና መልካም ሥራ መሥራት በመሆኑ የተጀመረውን መልካም ጅምር የሀገረ ስብከቱ ምግባረ ሠናይ ዋና ክፍሉ አጠናክሮ ሊቀጥልበት ይገባል፡፡
{flike}{plusone}