የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባደረገው ድጋፍ በቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት የተዘጉ 9 አብያተ ክርስቲያናት እንዲከፍቱ ማድረጉ ተገልጸ።

ሦስተኛውን ቀን የያዘው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 43ኛ መንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የየአህጉረ ስብከቱ ዓመታዊ የአገልግሎት አፈጻጸም ሪፖርቶች እየቀረቡ ይገኛሉ።
ከነዚህ በአዲስ የተቋቋመው የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ሪፖርት ያቀረበ ሲሆን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባደረገው ድጋፍ በቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት የተዘጉ 9 አብያተ ክርስቲያናት እንዲከፍቱ አድሮጓል በለዋል።
የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና ያቀረበ ሲሆን ከነዚህም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤትና በሥሩ ሉ ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት እንዲሁም ገዳማትና አድባራት ይገኙበታል።
በሌላ በኩል የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ባከናወነው የስብከተ ወንጌል አገለግሎት ከተመለሱት 187 የሌሎች ቤተ እምነት አባላት መካከል 6ቱ መምህራን የነበሩ መሆናቸውን በሪፖርቱ ገልጸዋል።