የአዲስ አበባ ሀገረ ስበከት ለአድባራትና ገዳማት የሒሳብ ሠራተኞች ሁለተኛ ዙር የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና መስጠት ጀመረ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሒሳብና በጀት ዋና ክፍል እየተዘጋጀ ሲሰጥ የቆየው የአድባራትና ገዳማት የሒሳብ ሠራተኞች የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና ለሁለተኛ ዙር ተጠናክሮና ተሻሽሎ ለሠልጣኝ ሠራተኞች እየተሰጠ መሆኑ ታወቀ፡፡
የሁለተኛው ዙር ሰልጣኝ ሠራተኞች ቁጥራቸው ሰላሳ የሚደርስ ሲሆን ሦስቱ ሠልጣኞች የሀገረ ስበከቱ ሠራተኞች ናቸው፡፡ ሠልጣኝ ሠራተኞች በሥልጠናው የሚቆዩት ለአንድ ወር ብቻ ሲሆን የመጀመሪያው ዙር ሠልጣኞች የሥልጠና ጊዜ ግን ለሁለት ተከታታይ ወራት የቆዬ ነበር፡፡ የሁለተኛው ዙር ሠልጣኞች የሥልጠና ጊዜ በአንድ ወር የተወሰነው የአድባራቱና ገዳማቱ ቁጥር በርካታ በመሆኑ ሁሉም የአድባራትና ገዳማት የሒሳብ ሠራተኞች በወቅቱና በጊዜው የሥልጠናው ተካፋዮች እንዲሆኑና የማዳራስ ተግባር ለመፈጸም ታስቦ የተደረገ መሆኑን ሥልጠናውን የሚሠጡት የሀገረ ስብከቱ ሒሳብና በጀት ዋና ክፍል ኃላፊ ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነ አብራርተዋል፡፡
የሁለተኛው ዙር ሥልጠና ካለፈውና ከመጀመሪያው ዙር ለየት ያለ ሲሆን ይህም ካለፈው ተሞክሮ በመነሳት የሥልጠናው ማንዋሎች በስፋትና በጥራት በመዘጋጀታቸው እንደሆነ ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነ አክለው ገልጸዋል፡፡
አክሮባል ቤዝ/GAAP የሒሳብ አያያዝ፣ ጥሬ ገንዘብ ቅበላና ጥሬ ገንዘብ ክፍያ ላይ ያልተመሠረተ ፕሪንሲፕል አካውንቲንግ ሕጐችን አካቶ፣ /GAAP/ ጀነራል አክሴፕትድ አካውንቲንግ መሠረት አድርጐ በሥራ ላይ የሚውል የአካውንቲግን ሥራን ኮምፒውተር አካውንቲግ ፕሪንሲፕል መሆኑን ባለሙያው አብራርተዋል፡፡
በመማር ማስተማር ሂደት ከምንፈልገው ነገር ለመድረስ ጠንክረን መሥራት ይገባናል በማለት ሠልጣኞቹን ሲመክሩና ሲያበረታቱ የተስተዋሉት ሊቀ ጠበብቱ የመዝገብ ጥቅምንም ሲገልፁ ያለ መዝገብ የሚሠራ ነገር የለም ብለዋል፡፡
የመጀመሪያ ዙር ሠልጣኞች ሠራተኞች የሥራ ውጤት በተመለከተ ተጨማሪ መብራሪያ ሲሰጡ ንብረት በማስገመትና የመጀመሪያ የዘመናዊ ሒሳብ አሠራር ሙከራ እያካሄዱ ናቸው ብለዋል፡፡ የተጀመረው ሥልጠናም የዘመናዊ ሒሳብ አሠራራችን ወደ ትክክለኛ መስመሩ እስኪገባ ድረስ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
{flike}{plusone}