የታኅሣሥ ፫ በዓታ ለማርያም ክብረ በዓል በአዲስ አበባ ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል
ከተከበሩ የተከበረች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ድንግል ማርያም በሦስት ዓመቷ ከእናቷና ከአባቷ ተለይታ ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት “በዓታ ለማርያም” በዓል ታኅሣሥ 3 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በጥንታዊቷ ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ሊቃውንት እና በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኦርቶዶክሳውያን በተገኙበት ተከብሯል።
ፎቶ eotc tv ና ተሚማ