የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ የዕረፍት መታሰቢያ ሥርዓተ ጸሎት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናወነ

የብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዕረፍታቸው መታሰቢያ የጸሎት መርሐ ግብር በመንበረ ጽባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናውኗል።
‎በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ፤ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የደቡብ ምሥራቅ ትግራይና የራያ አህጉረ ስብከት፣ ሊቀ ጳጳስ፣ በመንበረ ፓትርያርክ የቅርሳ ቅርስ ጥበቃና ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ሙዚየም መምሪያ የበላይ ኃላፊ እና የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባና ሐዲያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፣ሊቀ ትጉኃን ታጋይ ታደለ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጆችና የመንበረ ፓትርያርክና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ሐላፊዎች ፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንና የመንፈስ ልጆቻቸዉ በተገኙበት ተከናውኗል ።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ነሐሴ ፲/፳፻፬ ዓ/ም ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው የሚታወስ ነው።
በረከታቸው ይደርብን።
ፎቶ፦ ነቢዩ ሚኪያስ