የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በሆስፒታል ለሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች የሚውል 400 ሽህ ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ !!!
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን የባህር ዳር ሀገረ ስብከት በባህር ዳር ፈለገ ሕይወት ሆስፒታል ለሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች የሚውል 400 ሽህ ብር የሚገመት ድጋፍ አድርጓል፡፡
የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን
ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች በሆስፒታሉ በመገኘት ታካሚ የፀጥታ አካላትን ጎብኝተዋል፣ የህክምና መስጫ ግብአቶችንና አልባሳትንም ለሆስፒታሉ አስረክበዋል።
በድጋፍ ርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ብፁዕነታቸው ኢትዮጵያን ለመታደግ የተዋደቁና የሕይወት ዋጋ የከፈሉ፣ ሁሉ ክብር ይገባቸዋል ብለዋል።
አክለውም ሀገርና ሕዝብን ከጥፋት ለመከላከል ሲሉ ዋጋ እየከፈሉ ለሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች ኅብረተሰቡ አስፈላጊውን እንክብካቤና ድጋፍ እንዲያደርግም ጥሪ አባታዊ ጥሪ አስተላልፈዋል።
የሀገረ ስብከቱን የዓይነት ድጋፍ የተረከቡት የፈለገ ሕይወት ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ዐቢይ ስለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።