የቅዱስ ያሬድን ሕይወትና ሥራዎችን የሚያሳይ መንፈሳዊ ፊልም ዝግጅትን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጠ
በዋካ ኢንተርቴይመንት የሚሠራውን የቅዱስ ያሬድን ሕይወት እና ሥራዎች የሚያሳይ መንፈሳዊ ፊልም አስመልክቶ ከሊቃውንት ጋር ውይይት በማካሄድ መግለጫ ተሰጠ።
የቅዱስ ያሬድን ሕይወት እና ሥራዎች የሚያሳይ መንፈሳዊ ፊልም
በዋካ ኢንተርቴይመንት ተሠርቶ በ#EOTCTV ለማሣየት የታቀደውን እቅድ አስመልክቶ የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት እና ዋካ ኢንተርቴይመንት ከያሬዳውያን ሊቃውንት ጋር ውይይት በማድረግ መግለጫ ተሰጠ።
መግለጫውን ያቀረቡት ዶክተር አካለወልድ ተሰማ የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፊልሙን ለመሥራት ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ሲከናወን መቆየቱን ገልጸው። ፊልሙ በ15 ወራት እንደሚጠናቀቅ ገልጸዋል።ፊልሙ ተሠርቶ ሲጠናቀቅም በሊቃውንት ተገምግሞ እንደሚተላለፍ ተገልጿል።
በውይይቱ በብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት እና የአፋን ኦሮሞ መገናኛ ብዙኃን ቴሌቪዥን ማሰራጫ ድርጅት የበላይ ኃላፊ የምሥራቅና ሰሜን አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ የተከፈተ ሲሆን ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብረሃ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ረዳት ፕሮፌሰር ግርማ ባቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የኢኮኖሚ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የመምረያ ኃላፊዎች እና ያሬዳውያን ሊቃውንት ተገኝተዋል።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ሊቃውንት አጠቃላይ የፊልሙ ይዝት ምን መምሰል እንዳለበት ከዋካ ኢንተርቴይመንት አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል ።
በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ቃለ ምዕዳን አስተላልፈዋል።
©EOTC TV