የሥልጠናና የምክክር ጉባኤ ጥሪ
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተሻለ የአመራር ለውጥ ማስመዝገብ ይቻል ዘንድ ለሀገረ ስብከቱ፣ ለክፍለ ከተማ፣ ለገዳማትና አድባራት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ከመስከረም 26-30 ቀን 2018 ዓ.ም የሥልጠናና የምክክር መርሐ ግብር ተይዟል ፡፡
በዚህ መርሐ ግብር መሠረት በሥልጠናውና በምክክሩ የሚሳተፉ አካላት
1. በ26/01/2018 ዓ.ም የሀገረ ስብከታችን የዋና ዋና ክፍል ሐላፊዎችና ምክትል የክፍል ኃላፊዎች፣ የክፍለ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጆችና የሰው ሃብት አስተዳደር ሠራተኞች፣
ቦታ፦በሀገረ ስብከቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ፣
2. በ27/01/2018 ዓ.ም የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ዋና ፀሐፊዎች፣
ቦታ፦ #በቅ/ሥላሴ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ፣
3. በ28/01/2018 ዓ.ም የገዳማትና አድባራት ምክትል ሊቃነ መናብርትና የሰንበት ት/ቤት ሊቃነ መናብርት
ቦታ ፦ #በቅ/ሥላሴ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ፣
4. በ29/01/2018 ዓ.ም የገዳማትና አድባራት ሂሳብ ሹሞችና ም/ሒሳብ ሹምና የቁጥጥር ኃላፊዎችና ም/ቁጥጥር
ቦታ፦ #በቅ/ሥላሴ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ፣
5. በ30/01/2018 ዓ.ም የሀገረ ስብከትና የክፍለ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት ልዩ ልዩ ሠራተኞች
በሀገረ ስብከታችን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሥልጠናውንና ምክክሩ የሚካሄድ ይሆናል።
የሥልጠናው ሰዓትም ከጠዋቱ 2፡00-11፡00 ይሆናል ፡፡
ስለዚህ በወጣው መርሐ ግብር መሠረት በሥልጠናውና በምክክሩ የምትሳተፉ አካላት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በመለየት በሰዓቱ እንድትገኙ ሀገረ ስብከቱ በጥብቅ ያሳስባል።
የተሻለ የአመራር ለውጥ
ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት
