“እየተፈጠረብን ያለውን ችግር ለመፍታት ቅዱስ ሲኖዶስ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል” …ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

የአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በማኅደረ መለኮት ወይብላ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው እየተፈጠረብን ያለውን ችግር ለመፍታት ቅዱስ ሲኖዶስ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል” ሲሉ  አስታወቁ።

ብፁዕነታቸው በቦታው ተገኝተው ሕዝበ ክርስቲያኑን  ያፅናኑ እና ቡራኬ የሰጡ ሲሆን እየተፈጠሩ ያሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እስከ ሕይወት መስዋዕትነት እያስከፈለ የሚገኝ መሆኑን ገልጸዋል።

የተፈጠረውን ችግር ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ሪፖርት ማድረጋቸውን በመግለፅ ቅዱስ ሲኖዶስ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ብፁዕነታቸው አስታውቀዋል።

አክለውም ብፁዕነታቸው ምዕመናን አንድነታቸውንና ኅብረታቸውን በማጠናከር ጥያቄዎቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ማቅረብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ለተጨማሪ መረጃ የሀገረ ስብከቱን ማኅበራዊ ድረ-ገጾችን ይጎብኙ፣ like እና Join በማድረግ ይቀላቀሉ፣ ለሌሎችም  ሼር ያድርጉ!!!

1. ድረ-ገጽ:- www.addisababa.eotc.org.et
2. ፌስ ቡክ ገጽ:- www.facebook.com/AddisAbabaDiocese/
3. ተሌ ግራም ቻናል:- t.me/AddisAbabaDiocese