ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዎድሮስ ፓትርያርክ ዘግብፅ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለመጎብኘት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ አስታወቁ!!

e11

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዎድሮስ የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በ2008 ዓ.ም የሚከበረውን የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ በ2008 ዓ.ም መስከረም ወር ላይ ከግብፅ ኮፕቲክ ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋር በመሆን ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የጉብኝት ተግባር እንደሚያከናውኑ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሐምሌ 30 ቀን 2007 ዓ.ም በመንበረ ፓትርያርክ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ተገኝተው ቁጥራቸው ከ800 በላይ ለሚሆን የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ተወካዮች አስታውቀዋል፡፡
ቅዱስነታቸው ከዚህም ጋር አያይዘው የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከተመሠረተ ረጅም ዕድሜን ያስቆጠረ በመሆኑ ገዳማቱና አድባራቱ የቆየ ታሪካ አላቸው ብለዋል፡፡
የተሻለነና ዘመናዊ አመራርም ይታይባቸዋል በማለት የገለጹት ቅዱስነታቸው ለወደፊቱ  የእኛም ቤተ ክርስቲያን ወደ ተሻለ ደረጃ ትደርሳለች ብለን ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል፡፡

{flike}{plusone}