ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤልን በዓል ለማክበር ድሬዳዋ ገቡ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያ የሥራ ኀላፊዎች ዓመታዊውን የቅዱስ ገብርኤል በዓል ለማክበር ድሬዳዋ ገብተዋል።
ቅዱስነታቸው ድሬዳዋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ክቡር አቶ ከድር ጁሐር የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር ኮምሽነር ዓለሙ መግራ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ከፍተኛ የአስተዳደሩ ባለስልጣናት ክቡር መጋቤ ሠናያት ቀሲስ ኃይለ ማርያም ገብረ ሚካኤል የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የሀገረ ስብከቱ የየክፍል ኀላፊዎች የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች ካህናትና ዲያቆናት የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
©️ምሥራቅ_ሐረርጌ_ሀገረ_ስብከት_ጽቤት