ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትርያርክ ሁሉም ሰው ለሰላም የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፍ አሳሰቡ !!!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ሁሉም ሰው ለሰላም የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ለኢትዮጵያ አንድነት እና ለሕዝቡ ደህንነት እንዲሰራ  ጥሪ አስተላልፈዋል።

ቅዱስ ፓትርያርኩ ይህንን ጥሪ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ጃንሜዳ ባህር ጥምቀት ላይ በድሬዳዋ እና ጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም በ ውጭ ጉዳይ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ በብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ አማካኝነት ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

መተው ነገሬን ከተተው በሚለው በአበው ብሂል
እና በበዓለ ጥምቀት አስተምህሮ ላይ ተመሥርቶ ሁሉም ሰው በእውነተኛ ንስሐ መንፈስ ቅራኔን፣ ጥላቻን፣ በቀልን እና ቂምን እርግፍ አድርጎ በመተው ወደ ቀደመ ፍቅራችን መመለስ እንደሚገባ ቅዱስነታቸው  አሳስበዋል።

የቅዱስ ፓትርያርኩን አባታዊ መልዕክት በንባብ ያሰሙት ብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ ፓትርያርኩ አሁን ላይ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙና በቅርቡ ሕክምናቸውን አጠናቀው ወደ መንበረ ፕትርክናቸው እንደሚመለሱ አብስረው፣ በዓሉ የሰላም: የአንድነትና የፍቅር ይሆን ዘንድ ምኞታቸውን ገልጸዋል።

            በመ/ር ሽፈራው እንደሻው

ለተጨማሪ መረጃ የሀገረ ስብከቱን ማኅበራዊ ድረ-ገጾችን ይጎብኙ፣ like እና Join በማድረግ ይቀላቀሉ፣ ለሌሎችም  ሼር ያድርጉ!!!

1. ድረ-ገጽ:- www.addisababa.eotc.org.et
2. ፌስ ቡክ ገጽ:- አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት/Addis Ababa Diocese
3. ተሌ ግራም ቻናል:- t.me/AddisAbabaDiocese