ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ አሸባሪው ህወሓት በወልዲያ በርካታ ንፁሐንን በመግደልና ንብረት በመዝረፍ ከፍተኛ በደል መፈፀሙን አስታወቁ !!!
የሰሜንና የደቡብ ወሎ እንዲሁም የከሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ አሸባሪው ህወሓት በወልዲያ በርካታ ንፁሐንን መግደሉንና በንብረት ላይ ዘረፋ እና ውድመት መፈፀሙን አስታወቁ።
ብፁዕነታቸው አሸባሪው ቡድን በወልዲያ ከተማ በቆየባቸው ጊዜያት የከተማው ነዋሪ እህል ፣ መድኃኒት እና አስፈላጊ ነገሮችን ሳያገኝ መቆየቱን ገልፀዋል።
በተጨማሪም ከግለሰብ ኪስ ጀምሮ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን መዝረፋቸውን እና ማውደማቸውን አውስታውቀዋል።
ከፖለቲካ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን የቆሎ ተማሪዎችንና ማንኛውንም ሰላማዊ ነዋሪ በመረሸንና እናቶችንና ህፃናትን በመድፈር ከፍተኛ ኢሰብዓዊ በደል ማድረሱን ለኢቲቪ ገልፀዋል።
አክለውም እኔ ከፖለቲካ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለኝም ያሉት ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ለሐዋርያዊ አገልግሎት የሚጠቀሙበትን መኪና በዚሁ አሸባሪ ቡድን የተወሰደ መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል።
የተገኘው ድል የመላው ኢትዮጵያውያን ድል በመሆኑ የኢትዮጵያ አንድነት በዚሁ ስሜት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባውም ብፁዕነታቸው አስታውቀዋል።
Photo ፦ TMC
በመ/ር ሽፈራው እንደሻው