ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በዝውውርና በአዲስ ምድብ የተመደቡት የየክፍለ ከተማ ቤተ ክህነቱ ሥራ አስኪያጆች የተሰጣቸው ሐላፊነት ሹመት ሳይሆን የአገልገሎት ጥሪ መሆኑን ሳይዘነጉ እንዲያገለግሉ አሳሰቡ
ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በዝውውርና በአዲስ ምድብ የተመደቡት የየክፍለ ከተማ ቤተ ክህነቱ ሥራ አስኪያጆች የተሰጣቸው ሐላፊነት ሹመት ሳይሆን የአገልገሎት ጥሪ መሆኑን ሳይዘነጉ እንዲያገለግሉ አሳሰቡ።ብፁዕነታቸው ይህንን ያሉት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኙ ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ተዘዋውረውና በአዲስ ምደባ እንዲያገለግሉ ለተመደቡት ሥራ አስኪያጆች የእንኳን ደህና መጣችሁና የትውውቅ እንዲሁም የሥራ መመሪያ መስጫ መርሐ ግብር ላይ ነው።
በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባና ሀዲያና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳ፣ መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የሀገረ ስብከቱ ከፍተኛ የሥራ ሐላፊዎች፣ የየክፍለ ከተማ ቤተ ክህነቱ ሥራ አስኪያጆችና ሠራተኞች እንዲሁም የገዳማትና የገዳማት አስተዳዳሪዎች ተገኝተዋል።
መርሐ ገብሩ በጸሎት የተጀመረ ሲሆን
መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የተመደቡት ሥራ አስኪያጆችን አስተዋውቀዋል።
በዚህ መሠረት
አያይዘውም የሥራ ሐላፊነቱ የሕያው ቤተ መቅደስና የቅዱስ ወንጌል በቅንነትና በትጋት ለማገልገል መሆኑን አስታውሰው በዝውውርና በአዲስ መልክ በየክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት በሥራ አስኪያጅነት የተመደቡትን የሥራ ሐላፊዎች መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።
አክለውም በሀገረ ስብከቱ የሚገኙት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች በመልካም የሚመሯቸውን መሪዎች ካገኙ በእጅጉ የተጠናከረ ሥራ እንደሚሠሩ ተናግረዋል።
ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ በበኩላቸው ሹመት ሳይሆን የአገልገሎት ጥሪ ነው ያሉ ሲሆን ነገ ቦታው ለሌላ እንደሚሰጥ አስበን በጊዜያችን ቤተ ክርስቲያንን የሚመጥንና ኑሮየ ይበቃኛል ማለትን መሠረት ያደረገ አገልግሎት እንዲሰጡ አሳስበዋል።
አገልግሎታችን የመተካካት መሆኑን አስበንና የተጠራንበትን ጥሪ ተቀብለን ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን መሥራት ይኖርብናል ብለዋል።
