ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ የዐቢይ ጾም አገልግሎትን አስመልክተው ለገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች መመሪያ አስተላለፉ
ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባና ሀዲያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዐቢይ ጾምን አስመልክተው ለገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች መመሪያ አስተላለፉ።በትናትናው ዕለት በሀገረ ስብከቱ አዳራሽ በተከናወነው መርሐ ግብር ብፁዕነታቸው ጾሙ በረከት የምናገኝበት ታላቅ ሕይወት ጾም በመሆኑ የቤተ መቅደሱና የዐውደ ምሕረቱ አገልግሎት ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን በመጠበቅ በመልኩ በተጠናከረ ሁኔታ እንዲቀጥል አሳስበዋውል።
በተለይም ቅዳሴ ሰዓት እንዲሁም የቅዱስ ወንጌል አገልግሎት በተመለከተ በትጋትና በጥንቃቄ እንዲከናወን አዳራ ብለዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የሀገረ ስብከቱ ዋና ክፍል ሐላፊዎች፣ የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆች፣ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎችና ሌሎች የአገልግሎት መሪዎች ተገኝተዋል።
