ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ የሆሣዕና ካህናት ማሰልጠኛ ተቋም የማሰልጠኛዉን ደረጃ ለማሳደግ ለ G+5 ሕንጻ መሠረት ድንጋይ ባርከው አስቀመጡ

የሆሣዕና ካህናት ማሰልጠኛ ተቋም የማሰልጠኛዉን ደረጃ ለማሳደግ G+5 ሕንጻ መሰረት በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ ሀዲያና ስልጤ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጥር 4 ቀን ተቀምጧል።
የሆሣዕና ካህናት ማሰልጠኛ ተቋም በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ መመሪያ ሰጪነት አዲስ በማስገንባት ላይ የሚገኘውን ግዙፍ የማሰልጠኛዉ ማስፋፊያ ሕንፃ የግንባታ ሥራው በአጭር ጊዜ ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት መሆን እንዳለበት ዲያቆን ኢንጅነር ለዓለም ጥላሁን ገልጸዋል።
የሕንፃውን የመሠረት ቁፋሮ ሥራ ፣ የሕንጻው መሠረት የአርማታ ሥራ (Mat Foundation) በቅርቡ የሚጀመር ሲሆን ህንጻዉ የቢሮ ፣የመመገቢያ አዳራሽ፣ ላይብረሪ፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ማደሪያን እንደያዘ ገልጸዋል።
ዲያቆን ኢንጂነር ለዓለም ጥላሁን አክለውም የሆሣዕና ካህናት ማሰልጠኛ ተቋም በ600 ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፈውን ባለ አምስት ወለል G+5 ሕንፃ ክረምቱንና የኮንስትራክሽን ዕቃዎች መወደድን ተቋቁሞ በታቀደለት ጊዜ በተቀመጠ የጥራት ደረጃ መሠረት ሠርቶ ለማጠናቀቅ ቀን ከሌሊት እንደሚሰራ ለብሕንሳ ሚዲያ ክፍላችን ገልጸዋል።
በመጨረሻም ብፁዕነታቸዉ ሕንጻ በአጭር ጊዜ በተቀመጠዉ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በማጠናቀቅ የገጠሪቷን ቤተክርስቲያን የሚያገለግሉ ልጆቻችን ለማፍራት አንዱ መሳሪያ በመሆኑ፣በአጭር ጊዜ ለአገልግሎት ክፍት መሆን እንዳለበት ገልጸዉ ፣በዚህ ትውልድን የሚታደግ ፕሮጀክት ላይ የሁላችንም አሻራ በማስቀመጥ መስራት እንደሚጠበቅብን በአባታዊ መልዕክታቸዉ ገልጸዉ በብፁዕነታቸው ካለ ምእዳን መርሐግብሩ የፍጻሜውን አግኝቷል