ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ውይይት አደረጉ

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ውይይት አደረጉ።
በውይይታቸው ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕድ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በ1940 ዓ/ም የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ሲመሠረት መስራች ከሆኑ አብያተ እምነታት መካከል በቀዳሚ የምትጠቀስ መሆኗን የተሳ ሲሆን በሀገራችን ትውልዳዊና ሀገራዊ ሁለንተናዊ አገልግሎቶች ላይ ሰፊ ድርሻዋን እየተወጣች እንደምትገኝ በውይይቱ ተነስቷል።
በተጨማሪም የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሚለከታቸውን የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮችን አሰንተው ተወያያተዋል በቀጣይ መሰል ውይይቶችና ግንኙነቶች እንደሚቀጥሉ ተነግሯል።
በተናያዘም የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤው ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ታጋይ ታደለ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ከተመደቡ በኋላ ዘመኑን የዋጀ የቢሮ እድሳትና ገጽታ ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ባዩት ነገር በእጅጉ መደነቃቸውን ገልጸዋል።
በውይይት መርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕነታቸውና ሊቀ ትጉኃንን ጨምሮ መልአከ ምሕረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የሀገረ ስብከቱና የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሥራ ሐላፊዎች ተገኝተዋል።