ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ በሀገረ ስብከቱ በሁሉም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ተቋማዊ የሆነ የበይነ መረብ ሚዲያ እንዲቋቋም መመሪያ አስተላለፉ።
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ በሀገረ ስብከቱ በሁሉም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ተቋማዊ የሆነ የበይነ መረብ ሚዲያ እንዲቋቋም መመሪያ አስተላለፉ።
ብፁዕነታቸው ይሄን ያሉት “መገናኛ ብዙኃን ለቤተ ክርስቲያን ተሌእኮ ” ቀሚሙም መሪ ቃል ሀገረ ስብከቱ ከTakeoff Digital ከተባለ ድርጅት ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የሦስት ቀናት ሥልጠና መርሐ ግብር ተዘጋጀው ላይ ነው።
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የተዋሕዶ ሚዲያ ማእከል የበላይ ጠበቂ እንዳሉት ሀገረ ስብኩቱ ሥራዎች ውጤታማና የተሻለ ለውጥይመጣ ዘንድ በሥልጠና በማገዝ አስፈላጊነቱን በማመኑ በትኩረት እየሠራበት እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ አክለውም የሚዲያን አስፈላጊነት ለቤተ ክርስቲያን ምኖያህነ እንደሆነ ያብራሩ ሲሆን “በዚህ
“በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሚዲያን መጠቀምና ምን አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው” ብለዋል።
ለዚህም የሀገረ ስብከቱንም የአገልግሎት እንቅስቃሴ ብሎም የኦርቶደክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችንን እውነተኛ መልክ በጠበቀ መልኩ ሚዲያን ለመጠቀም እንዲቻል ሀገረ ስብከቱ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን ተናግረዋል።
ለዚህም አስፈላጊነቱን በማመን ከሁሉም 251 ገዳማትና አድባራት የተውጣጡ ሁለት ሁለት በድምሩ 500 ለሚዲያ ቅርብ የሆኑ አገልጋዮች ን ያሳተፈ ሥልጠና መሰጠቱን ለዚህ ሁነኛ ማሳያ ነው ብለዋል።
ሥልጠናው የቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ወንጌል ለትውልዱ ለማስተላለፍ ይቻል ዘንድ የሚዲያ አገልጋዮችን ቁጥር
እንደሚጨምር አስታውሰው ሥልጠናው በሚለካ ውጤት መታጀብ ስላለበት ከዚህ በኋላም ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።
ከዚህ በኋላም ይላሉ ብፁዕነታቸው በሀገረ ስብከቱ የሚገኙ ሁሉም ገዳማትና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ተቋማዊ የሆነ የበይነ መረብ ሚዲያ (የማኅበራዊ ድረ ገጽ ) ማቋቋም እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
በመጨረሻም ብፁዕነታቸው ለዚህ መርሐ ግብር መሳካት ድርሻውን የተወጡትን አካላት ያመሰገኑ ሲሆን በተለይም የTakeoff Digital ድርጅት ባለቤትና መሥራችን ዲ/ን ሰውመሆን ክንዱንና ጓደኞቹን አመስግነዋል።
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ በቤተ ክርስቲያን ሚዲያ አገልግሎት ዘርፍ ምዕራብ አርሲ ሻሸመኔ ሀገረ ስብከት ከነበሩበት ወቅት ጀምሮ ሚዲያን በቤተ ክርስቲያናዊ አገለግሎታቸው ያላመዱና ያቋቋሙ ሲሆን በተለይም ብፁዕነታቸው በበላይ ጠበቂነት የሚመሩት የተዋሕዶ ሚዲያ ማእከል ለዚህ ሁነኛ አብነት መሆኑ ይነገራል።
Source:-አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ