በፌዴራል የሃይማኖት ተቋማት ባለመግባባት ጎዳዮች ዙሪያ የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስፈን በአይነቱ የተለየ ውይይት እየተካሄደ ነው

00008

በሃይማኖት ተቋማት ያለመግባባት ጎዳዮች መሠረታዊ የመፍትሔ አቅጣጫ ዴሞክራሲያዊነትና ዘመናዊ አሰራርን ለማስፈን በሚል ርዕስ የፌዴራል የሃይማኖቶች ጎዳዮች ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጋር በመሆን ቁጥራቸው ከ1000 በላይ ለሚደርስ የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ተወካዮች ከነሐሴ 29 ቀን 2007 ዓ.ም  እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2007 ዓ.ም ድረስ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ በአይነቱ ልዩ የሆነ ውይይትና ምክክር እየተካሄደ ሲሆን በመጀመሪያ ጉባኤው በጸሎት ተከፍቶ የአዲስ አበባ የሃይማኖቶች ጉዳይ ሰብሳቢ የሆኑት ሊቀ ተጉሃን ታጋይ ታደለ ባስተላለፉት የመግቢያ ንግግር የሰው ልጅ በዓለም ትልቁ ስኬት በሰላም እና በፍቅር አብሮ መኖር መሆኑን፣ ያለ ሰላም የግለሰብም ሆነ የሀገር እድገር ሊረጋገጥ የማይችል መሆኑን፣ ኢትዮጵያ የስልጣኔ ምንጭና የሰው ዘር መገኛ መሆኗን፣ ለዘመናት ጠላቶቿን ያሳፈረች መሆኗን ጭምር በመግለጽ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆነ በመቀጠልም የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ባስተላለፉት የመክፈቻ ንግግር እና ባቀረቡት የጥናት ውይይት መሠረት የውይይቱ ዋና አላማና መሠረታዊ ጉዳይ ሁከትንና ብጥብጥን በማስወገድ ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት ነው፡፡
ለሁከትም ሆነ ለብጥብጥ መነሻዎቹ በቡድንም ሆነ በግል አፍራሽ ተልዕኮን በመያዝ በሃይማኖት ሽፋን ሁከትንና ብጥብጥን የሚያራምዱ ኃይሎች ናቸው፤ ወሬ የሚያመላልሱና የጨለማ መንገደኞች የሆኑ ክፍሎች አፍራሽ ተልዕኮቸውን እንዲያስወግዱ ማድረግ አለብን፤ እኔ ብቻ አልፎልኝ ሌላው እየተጎዳ መኖር አለበት የሚል አስተሳሰብ መሠረተ ቢስ አስተሳሰብ ነው፤ አለመግባባትን በማስወገድ የዕርቅ ባህልን ማዳበር አለብን፤ አንዱ ሃይማኖት ሌላውን ሃይማኖት የመጋፋት ተግባር አይፈፅምም፤ ነገር ግን ራሱን ሊከላከል ይችላል፤
የአስተዳደር እና የተጠያቂነትን ቁመና መፈተሽ አስፈላጊ ነው፤ እየተፈጠረ ያለው ችግር በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈ ሳይሆን እኛው ራሳችን የፈጠርነው ችግር ነው፤ እኛው የፈጠርነውን ችግር መፍታት ያለብን እኛው ራሳችን ነን፤ የፖለቲካና የእርዕዮተ ዓለም ፍላጎት አለኝ የሚል አካል ካለ ይህንን አስተሳሰብ በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ማራመድ አይገባውም፤ ድብቅ አላማ ላላቸው ክፍሎች ተጋላጭ ሳንሆን የራሳችንን ችግር በራሳችን መፍታት አለብን፤ የቅሬታ ማስተናገጃ ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ነው በማለት ሚኒስትሩ በጥናታዊ ጽሑፍ የተደገፈ መልዕክታቸውን ሰፋ አድርገው ካስተላለፉ በኋላ ውይይቱ ቀጥሏል፡፡
ቀጣዩን የውይይት ሐሳብና ጥናታዊ መግለጫዎችን እየተከታተልን እናቀርባለን፡፡  

{flike}{plusone}