በጉራጌ ሀገረ ስብከት በአበሽጌ ወረዳ የሚገኘው የደብረ ከርቤ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተመርቆ ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ
በትናንትናው ዕለት አዲሱ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተባርኮ ታቦተ ህጉ ወደ መንበረ ክብሩ ገብቷል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በጉራጌ ሀገረ ስብከት በአበሽጌ ወረዳ የሚገኘው የደብረ ከርቤ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ ሥራአስኪያጅ መጋቤ ስብሐት ሣህሉ ተሰማ ፣ የሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ኃላፊዎችና ልዩ ልዩ ሠራተኞች፣ከወረዳው የመጡ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የአካባቢው ምዕመናን እና ከአዲስ አበባ የሄዱ የአከባቢው ተወላጆች በተገኙበት የካቲት 20/2013 ዓ.ም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አሄጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተባርኮና ተመርቆ ታቦተ ህጉ ወደ መንበረ ክብሩ የገባ ሲሆን በዛሬው ዕለት የካቲት 21/2013 ዓ.ም ቅዳሴ ቤቱ ተከብሮ የዋለ ሲሆን ከሰዓት በኋላ በነበረው መርሐ ግብር ብፁዕነታቸው በእዣ ወረዳ የቆጠርገድራ መካነ ቅዱሳን ኪዳነ ምሕረት ገዳም የአብነት ት/ቤት ሕንፃ ባርከው መርቀዋል፡፡
ሕንፃው የተማሪዎች መማሪያ፣ መመገቢያ እና ንጽሕና መጠበቂያን የሚያካትት ሲሆን ለግንባታው 2.2 ሚሊዮን ብር ወጭ ያደረገውና ምረቃውን ያስፈጸመው ማኅበረ ጽዮን መንፈሳዊ የጉዞ ማኅበር ነው፡፡
የአብነት ት/ቤቱ ከ2005 ዓ/ም ጀምሮ በርካታ ምሁራንን ያፈራ ሲሆን አሁንም ተጠናክሮ በመቀጠል ታዋቂ የሀገረ ስብከቱ የመንፈሳዊ ትምህርት ሆኗል፡፡
በሌላ ዜና በዚሁ ሣምንት ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አሄጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንትና የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ከብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ጌዴኦ እና ቡርጂ ዞኖች ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ፣ ከብፁዕ አቡነ ናትናኤል የምሥራቅ ወለጋ ፣ የሆሮ ጉድሩ ወለጋ እና የምዕራብ ሸዋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ከብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የከምባታ ሀዲያና ስልጤ እና የደቡብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጋራ በመሆን በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት በሐመር ወረዳ ቡስካ ቀበሌ በተገደመችው ደብረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ወሙሴ ጸሊም ገዳም ባርከው የመረቁ ሲሆን ከ690 በላይ የሐመር ብሄረሰብ ተወላጆች የሥላሴ ልጅነትን እንዲያገኙ ሐዋርያዊ አገልግሎት ተሰጥተው መመለሳቸው እና አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ራሱን ችሎ በራሱ ሊቀ ጳጳስ መመራት ከጀመረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለ2 ቀናት የቆየ እጅግ የተሳካ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጽርሐ ተዋሕዶ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ማካሄዳቸው ይታወሳል።
በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ
ፎቶና የዜናው ምንጭ፦ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት
የሀገረ ስብከታችን ፌስቡክ እና ድረ-ገጽ አድራሻ like, Follow and share በማድረግ፤ ሌሎችም like, Follow and share እንዲያደርጉ በመጋበዝ የቤተ ክርስቲያን ልጅነትዎ ይወጡ!!!
የሀገረ ስብከታችን ማኅበራዊ ድረ ገጽ፦
- ድረ-ገጽ:- www.addisababa.eotc.org.et
- ፌስ ቡክ ገጽ:- አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አይቲና ዶክሜንቴሽን /Addis Ababa Diocese IT& Documentation
- ተሌ ግራም ቻናል:- t.me/AddisAbabaDiocese
- ዩትዩብ ቻናል:- www.youtube.com/channel/UCtYqL7fu87AVTGHaZDPToFg