በዓለ ጥምቀትን አስመልክቶ የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት መሪዎችና የአድባራት አስተዳዳሪዎች ከክፍለ ከተማው ሥራ አስፈጻሚና ጸጥታ ዘርፍ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ተገለጸ
በዓለ ጥምቀትን አስመልክቶ በቦሌ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት መሪዎችና አድባራት አስተዳዳሪዎች ከክፍለ ከተማው ሥራ አስፈጻሚና ጸጥታ ዘርፍ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ተገለጸ።
በየዓመቱ የሚከበረው የጥምቀት በዓል በአዲስ አበባ በ65 የታቦታት ማደሪ ባሕረ ጥምቀት የሚከበር ሲሆን በዓሉ በሰላምና ዓላማውን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል።
በዛሬው ዕለት የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ና ከክፍለ ከተማው የመንግሥት መዋቅር ጋር በመሆን የተካሔደው ውይይት በዓሉ ፍጹም መንፈሳዊና ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር ምክክር የተደረገበት ነው ተብሏል።
በውይይቱ ላይ የቦሌና ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ሩፋኤል የማነ ብርሃን፣ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ክብርት ወ/ሮ ዓለምፀሐይ ሽፈራው፣ ኮሚሽነር አድማሱ ፣ ክፍላተ ከተማው ቤተክህነት ስር ከሚገኙ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና የአገልግሎት መሪዎች ተገኝተውበታል።
መረጃውን ያደረሰን የቦሌና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ነው።
©የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ