በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ክ/መ/ፓ/ጠ/ፅ/ቤት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የአዲስ አድማስ ጋዜጣ አዘጋጆች የቤተክርስቲያኒቱን ስም ከማጥፋት እንዲታቀቡ አሳሰበ

አዲስ አድማስ ጋዜጣ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የፓትርያሪኩን እገዳ ተቃወሙ በሚል ርዕስ ቅዳሜ የካቲት 14/2007 ዓ.ም በቅጽ 14 ቁጥር 788 በጋዜጣው ፊት ለፊት ላይ አሳትሞ የቤተክርስቲያኒቱን ስም ማጥፋቱ አይዘነጋም፡፡ ይህንን ተከትሎም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለሰንበት ትምህረት ቤቶች ማደራጃ በቁጥር 3092/546/07 በቀን፡- 19/06/07 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ የካቲት 8 ቀን 2007 ዓ.ም ሀገረ ስብከቱ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጋር በመተባበር ለግማሽ ቀን ያህል በተካሄደው ስብሰባ  በጠቅላላ በሰንበት ትምህርት ቤቱ እየተሠራ ስላለው ሥራ ለመወያየት ከ7ቱም ክፍላተ ከተማ በተውጣጡ የሰንበት ት/ቤቶች የሥራ አመራር አባላት ጋር ውይይት ማድረጉን ገልፆ ነገር ግን በአዲስ አድማስ ጋዜጣ የወጣው ጽሑፍ በፍፁም ከእውነት የራቀና ከጉባኤው ይዘትና ዓላማ ውጭ መሆኑን ለሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ አሳውቋል፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃም  የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በቀረበለት መነሻነት የሚከተለውን ደብደቤ በአድራሻ ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ፅፏል፡፡

ስብሰባው በተካሄደበት ዕለት ከሀገረ ስብከቱ ጋዜጠኛ በስተቀር ምንም ዓይነት የመንግስም ይሁን የግል ሚይዲያ ያልተጠራ ሲሆን በወቅቱ ስለነበረው የስብሰባው ይዘት ግን በዕለቱ በሀገረ ስብከቱ ድረ ገፅ አየር ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡ሐቁና እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ነገር ግን ባልተጠሩበትና በሌሉበት ነገር ላይ ያልሆነውን ነገር ሆኖ ብሎ መናገር ከሚድያ ስነ ምግባር ውጭ ከመሆኑም ባሻገር የታሪካዊቷንና ጥንታዊቷን ቤተ ክርስቲያን መዋቅር ዘልቆ ገብቶ ስም ማጥፋት በአገሪቱ ሕግ መሠረት በወንጀል የሚያስጠይቅም ጪምር መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳልን፡፡

{flike}{plusone}