በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት 14 የዋና ከፍል ኃላፊዎች ሹመት ሰጠ
የአዲሶቹ የሥራ ኃላፊዎች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ቀረቧል፡-
- መጋቤ ጥበባት ሲያምር ተ/ማርያም የአስተዳደር ዋና ክፍል ሓላፊ
- ሊቀ ኅሩያን ሰርፀ አበበ የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ ዋና ክፍል ሓላፊ
- ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነ የሒሳብና በጀት ዋና ክፍል ሓላፊ
- መልአከ ብርሃናት ፍስሀ ጌታነህ የቁጥጥር አገልግሎት ዋና ክፍል ሓላፊ
- መ/ር ዓይናለም ተጫነ የዕቅድና ልማት ዋና ክፍል ሓላፊ
- መ/ር ቀፀላ ጥላሁን የሕግ አገልግሎት ዋና ክፍል ሓላፊ
- መ/ር ቀለመወርቅ ዓለሙ የሰበካ ጉበኤ ዋና ክፍል ሓላፊ
- መ/ር ኀይለ እግዚእ የትምህርት እና ስልጠና ዋና ክፍል ሓላፊ
- መ/ር ሲሳይ ኦብሴ የቅርሳቅርስ ዋና ክፍል ሓላፊ
- አባ ገብረ እግዚአብሔር ገ/ጊዮርጊስ የካህናት አስተዳደር ዋና ክፍል ሓላፊ
- መጋቤ ሃይማኖት መሠረት አያሌው የጠቅላላ አገልግሎት ዋና ክፍልሓላፊ
- መምህር ሱራፌል ተፈራ የሰንበት ት/ቤቶች ዋና ክፍል ሓላፊ
- መጋቤሐዲ ስለማ በየነ የምግባረ ሠናይ ዋና ክፍል ሓላፊ
- መልአከ ሰላም ልዑል በላይ የመንፈሳዊ ፍርድ ቤት ሓላፊ በመሆን ተሹመዋል፡፡
በሌላ ዜና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የቀረቡለትን ቅሬታዎች መፍታት መቻሉን ገልጿል።
ኮሚሽኑ ይህንን አስመልክቶ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስከያጅ መ/ር ይቅርባይ እንዳለ ጋር ነሐሴ ፣ 2/2010ዓ.ም በጋራ መግለጫ ሰጥቷል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በአዲስ አበባ በተለያዩ ገዳማትና አደባራት ሲያገለግሉ የነበሩ ካህናትና ልዩ ልዩ አገልጋዮች የተለያዩ አስተዳደራዊ በደል ደርሶብናል በማለት ያቀረቡትን ቅሬታ ተከትሎ ነው መፍታት የተቻለው በማለት የኮሚሽኑ ኃላፊ አቶ ወንድምነህ ዘውዴ በመግለጫው አብራርተዋል።
በዚህም እስከ 300 የሚደርሱ በደል የደረሰባቸውን አካላት እልባት በመስጠት ወደ ስራቸው በመመለስ ላይ መሆናቸውንም ጨምረው ተናግረዋል።
የደረሱት በደሎች ኮሚሽኑ ሲገልጽ ካህናት፤ልዩ ልዩ አገልጋዮችና የተለያዩ አካላት ከስራ መታገድ፣ ከደምወዝ መቀነስ እንዲሁም አግባብነት የጎደለው የቦታ ዝውውርም ከቀረቡ ቅሬታዎች ለአብነት ተጠቅሰዋል።
በዚህም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቅድስ ፓትርያርክ ጋር በጋራ በመሆኑ ችግሮች የተፈቱ ሲሆን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽቤት ኃላፊ መ/ር ይቅርባይ እንዳለ ለኮሚሽኑ ምስጋና አቅርበዋል።
በደሉ የደረሰው ቅድስት ቤተ ክርስቲያኗ ባስቀመጠቻቸው የሰራ ኃላፊዎችና ተወካዮች ሲሆን በዚህም 14 በደል ያደረሱ አካላት ከስራቸው እንዲነሱ በማድርግ አዲስ ኃላፊዎችና ተተክተዋል ብለዋል።
ምንጭ፡-የኢ/መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት
አዲስ የሥራ ኃላፊዎቹ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው የዝግጅት ክፍላችን ይመኝላቸዋል፡፡