በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአራዳ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ጽ/ቤት በሥሩ ካሉ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በልማት ዙሪያ ውይይት አካሄደ
መስከረም 29/1/06 ዓ.ም በክፍለ ከተማው ሥር ከሚገኙ አስተዳዳሪዎች፤ ፀሐፊዎች፤ቁጥጥሮች፤ሒሳብ ሹሞችና ሰባክያነ ወንጌል ጋራ ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን በዚሁ ስብሰባ ላይ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትያርክ ረዳት ሊቀ ጳጳስ እና የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተገኝተዋል፡፡
ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ ስለ ክፍለ ከተማው አስመልክተው ሰፊ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በልማትና በመልካም አስተዳደር እንዲሁም በስብከተ ወንጌል ላይ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡በመሆኑም ቀደም ሲል የተቋቋሙት የልማትና እና የስብከተ ወንግል ኮሚቴዎች ባዘጋጁት ጽሁፍ ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡
አዲሱ ለሚሰራው G+5 የክፍለ ከተማው ህንፃ ሊያሠሩና ሊያሰተባብሩ የሚችሉ ኮሚቴዎች ቀደም ሲል መዋቀራቸው ይታወቃል፡፡
እነዚህም 5 ከክፍለ ከተማው ገዳማትና አድባራት፤2 ከክፍለ ከተማው ጽ/ቤት በድምሩ 7 ሰዎች ሲሆኑ እነዚህ ኮሚቴዎች ህንፃውን ለማሠራት ገዳማትና አድባራት፤በጎ አድራጊ ግለ ሰዎችና ድርጅቶች በማስተባበር ሥራው በመጪው 2006ዓ.ም ተጀምሮ በ2007 እንዲጠናቀቅ በክፍለ ከተማው መሪነት ከፍተኛ የሆነ ሥራ በመሠራት ላይ የገኛሉ፡፡
ህንፃው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅም ለቢሮና ለሁለ ገብ አገልግሎት ሊውል እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡በአሁኑ ሰዓት የህንፃው ዲዛይን አልቆ ሥራው ለመጀመር ከሚመለከታቸው አካላት ፈቃድ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡
እንደዚሁም በስብከተ ወንጌል ዙሪያ በኮሚቴዎች ተዘጋጅቶ የቀረበው ረቂቅ ሰነድ ሰፊ ውይይት ከተካሄደበት በኋላ ለሚቀጥለው ሰፋ ባለው መልኩ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ ሃሳብ ተሰጥቶበታል፡፡
ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር ለሚገኙት ገዳማት እና አድባራት እንደየ አቅራቢያቸው ተመድበው የአንድነት ጉባኤው በሚካሄድበት ወቅት ካህናትን እና ምዕመናንን ያቀራረበና ለስብከተ ወንጌል መስፋፋት መነቃቃትን የፈጠረ ጉባኤ እንደነበረ ይታወቅል፡፡ ይሁን እንጂ በሀገራችን አንዱ የጀመረውን መልካም ሥራ ተተኪው የማስቀጠል ልምድ ባለመኖሩ የአንድነት ጉባኤው ተቋርጦ ቆይቶ ነበር፡፡ ነገር ግን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለ7 ክፍለ ከተማ ከተከፈለ በኋላ የአራዳ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ጽ/ቤት የአንድት ጉባኤው ለስብከተ ወንጌል መስፋፋት ካህናቱን እና ምዕመናንን ለማቀራረብና በሃይማኖታቸው ፀንተው እንዲኖሩ አስፈላጊ በመሆኑ በክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስኪያጅ ሰብሳቢነት በተደረገው የሰባክያነ ወንጌል ጥምር ስብሰባ የአንድት ጉባኤው ጠንካራ ጎን እና ደካማ ጎን በስፋት ውይይት ከተደረገበት በኋላ የአንድነት ጉባኤው ለስብከተ ወንጌል መስፋፋት ጠቃሚ መሆኑ ስለታመነበት በክፍለ ከተማው የስብከተ ወንጌል መምሪያ ኃላፊ የሚመራ የስብከተ ወንጌል መስፋፋት አጋዥ ኰሚቴ ተመርጦ ሥራ በመጀመር የአንድነት ጉባኤው እንዲጀመር ገዳማት እና አድባራትን እንደየ አቅራቢያቸው በመመደብ ላይ ይገኛል፡፡ {flike}{plusone}