በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር ለሚገኙ ገዳማትና አድባራት አዲስ ለሚቀጠሩ የአብነት መምህራን ውድድር ተካሄደ
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሥሩ ለሚገኙ አድባራትና ገዳማት የአብነት መምህራንን አወዳድሮ ለመቅጠር ባወጣው መርሐ ግብር መሰረት ፈተናውን ያለፉ መምህራን 32 መሆናቸው ተገጸ፡፡
በሀገረ ስብከቱ የትምህርት ክፍል ዋና ክፍል ኃላፊ ሊቀ ማዕምራን ብርሃነ መስቀል ገበየሁን ጠይቀን እንደተረዳነው እነዚህ መምህራን በድጓ፣ በቅዳሴ ፣ በአቋቋም፣ በቅኔ፣ በዝማሬ መዋሥዕት፣ በብሉያት እና በሐዲሳት ተወዳድረው የተሻለ ውጤት በማምጣታቸው ነው ያለፉት በማለት ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም ሀገረ ስበከቱ ውድድሩን ያዘጋጀውቱ በሀገረ ስብከቱ ሥር ላሉ አድባራትና ገዳማት በመምህርነት ተመድበው እንዲያገለግሉ ቀደም ሲል ማስታወቂያ አውጥቶ የነበረ ሲሆን፣ በዚሁ መሰረት የሀገረ ስበከቱ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ መምህር ኃይለ ማርያም አብርሃን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ የክፍል ኃላፊዎች በከፊል በታዛቢነት በተገኙበት እና በአዲስ አበባ አሀገረ ስብከት ሥር ያሉ አድባራትና ገዳማት በመምህርነት ከሚገለግሉ በእውቀታቸው የተመሰገኑ ፈታኞች መምህራንን በመጋበዝ ውድድሩ እንደተከናወነ ውጤቱ ወዲያው መነገሩ ተፈታኞችንም ሆነ ፈታኝ መምህራንን ማስደሰቱን ለመረዳት ችለናል፡፡
ከሊቃውንተ ቤተ ከርስቲያን ፈታኝ በመሆን የተገኙ መምህራን
1.ሊቀ ጉባዔ አባ ገ/ማርያም ጌጡ
2.መ/ር መንግሥቱ ገብረ አብ
3.መ/ ገብር መድኅን ገ/ኢየሱስ
4.መ/ምስጢር ዘራአ ዳዊት ተገኘ
5.መ/ብሉይ ዕዝራ ለገሠ
6.ሊ/ጠበብት ኤልያስ መኮንን
7.ሊ/ጠበብት ጌትዬ ተ/ጻድቅ
8.ሊ/ጠበብት ፀጋዬ ኃ/ወይን
9.መ/ር ሙሉጌታ ፀጋ
10.መ/ር ጥዑመ ልሳን ድረስ
ከአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት በፈተናው ላይ የተገኙ ፈታኝ መምህራን እነዚህ ሲሆኑ ከአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች በታዛቢነት የተገኙት ደግሞ፡-
1.መላከ ገነት አባ ተክለ ማርያም አምኜ የአስኮ ደ/ገነት ቅ/ገብርኤል አስተዳዳሪ
2.ሊቀ ሊቃውንት አባ ወ/ማርቆ ገ/እግዚአብሔር የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም አስተዳዳሪ
3.ሊቀ ብርሃናት ክለ ማርያም መንገሻ የላፍቶ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ
4.መ/ብርሃን አእምሮ ምስጋናው የቀራኒዮ መድኀኒአለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ
5.መ/ሰላም ሰለሞን ዋሴ የሴኤመሲ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ
የሀገረ ስብከቱን ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ የክፍል ዋና ኃላፊዎች በጉባዔው ላይ ተገኝተዋል
1.መ/ር ኃይለማርያም አብርሃ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ
2.ሊቀ ማእምራን ብርሃነ መስቀል ገበየሁ የትምህርትና መሰልጠኛ ዋና ክፍል ኃላፊ
3.መ/ር ሣህለማርያም ወዳጄ የሰው ኃይል አስተዳደር ዋና ክፍል ኃላፊ
4.ላዕከ ወንጌል በእደማርያም ይትባረክ የስብከተ ወንጌል ዋና ክፍል ኃላፊ
5.መ/ር አሉላ ለማ የምግባረ ሰናይ ዋና ክፍል ኃላፊ
6.መ/ር ዮሴፍ ወዳጆ የትምህርትና ማሰልጠኛ ክፍል ኃላፊ፡-
በመሆን በብፁዕ አባታችን አቡነ ቀለሚንጦስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ሊቀ ጳጳስ የጉራጌ ስልጤ ሐድያና ከንባታ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ጥብቅ አመራር ሰጪነትና ክትትል ሁሉም የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣታቸውነ የዝግጅት ክፍላችን መገንዘብ ችሎል፡፡ የፈተናውን ሁኔታ በተመለከተ የሀገረ ስበከቱ ትምህረት ክፍል ለብፁዕ አባታችን አቡነ ቀለሚንጦስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስበከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ሊቀ ጳጳስ የጉራጌ ስልጤ ሐድያና ከንባታ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ያቀረቡትን ሪፖርት ከዚህ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡
ለብፁዕ አባታችን አቡነ ቀለሚንጦስ
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ሊቀ ጳጳስ የጉራጌ ስልጤ ሐድያና ከንባታ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡ – ሪፖርት ማቅረብን ይመለከታል፡፡
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ አድባራትና ገዳማት የአብነት መምህራን አወዳድሮ ለመቅጠር ባወጣው መርሐ ግብር መሠረት ከተመዘገቡ 92 መምህራን ማስረጃቸው ሲጣራ 26ቱ መምህራን በዚሁ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር በልዩ ልዩ ሥራ የተሠማሩ ስለሆነ ሥራ ለሌላቸው ቅድሚያ በመስጠት 56 መምህራን ለፈተና እንዲቀርቡ የተደረገ ሲሆን ከነዚህም 23 በራሳቸው ፈቃድ በተለያየ ምክንያት ራሳቸውን ከውድድር ሰርዘው 43 መምህራን ብቻ ተፈትነው
1.ከድጓ 10 ተፈትነው ያለፉ8 ያላለፉ2
2.ከቅዳሴ 13 ተፈትነው ያለፉ 10 ያላለፉ3
3.ከአቋቋም 13 ተፈትነው ያለፉ 13 ያላለፈ የለም
4.ከቅኔ 4 ተፈትነው ያለፉ 4 ያላለፈ የለም
5.ከዝማሬ መዋስዕት 4 ተፈትነው ያለፉ 4 ያላለፈ የለም
6.ከብሉያት 2 ተፈትነው ያለፉ የለም ያላለፉ2
7.ከሐዲሳት 6 ተፈትነው ያለፉ3 ያላለፉ3 ሲሆኑ በጠቅላላው ቢቢህ ፈተና ያለፉ 32 ያላሉፉ 11 ናቸው፡፡
ስለሆነም በውጤታቸው መሠረት ባለው ክፍት ቦታ ይመደቡ ዘንድ የፈተኞችን ቃለ ጉባኤና የተፈታኞችን ስም ዝርዝር እንደየውጤታቸው በቅድም ተከተል እስከፈተናው 10 ገጽ ያቀርብኩ ስለሆነ ለአመዳደቡ አባታዊ አመራር ተሰጥቶበት እንዲፈፀም ቢሆን መልካም ነው በማለት ይህን አጭር ሪፖርት በትህትና አቀርባለሁ፡፡
ሊቀ ማእምራን ብርሃነ መስቀል ገበየሁ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ትምህርትና ማሰልጠኛ ዋና ከፍል ኃላፊ
{flike}{plusone}