በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ፣ ለአድባራትና ገዳማት ተወካዮች መዋቅርዊ የአሠራር ለውጥ እና አደረጃጀት ላይ ውይይት በመካሄድላይ ነው
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአራዳና ጉለሌ ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሥር ለሚገኙ የ20 አድባራት እና ገዳማት ተወካዮች በመዋቅራዊ አደረጃጀት ረቂቅ ሰነድ ዙሪያ ከህዳር 27 – 28 ቀን 2006 ዓ.ም የሚቆይ ስልጠና እየተሰጣቸው የሚገኙ ሲሆን የሰልጣኞች ብዛት 320 ይደርሳል፡፡ በሀገረ ስብከቱ የጥሪ ደብዳቤ መሠረት ከእያንዳንዱ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የሚወከሉት ተሳታፊዎች ጠቅላላ ብዛት 16 ሲሆኑ የውክልናቸው ኹኔታ፡-
• ከካህናት – 1
• ከዲያቆናት – 1
• ከመዘምራን – 1
• ከአብነት መምህራን – 2
• ከስብከተ ወንጌል – 1
• ከሰንበት ት/ቤት – 2 (ሰብሳቢና በሰበካ ጉባኤው የሰንበት ት/ቤቱ ተወካይ)
• ከምእመናን – 4 (የሰበካ ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢን ጨምሮ)
• አስተዳዳሪ፣ ጸሐፊ፣ ሒሳብ ሹም፣ ቁጥጥር – 4 ናቸው፡፡
በአጠቃላይ ከ2,662 በላይ ተሳታፊዎች በመዋቅራዊና የአሠራር መመሪያ ጥናት ረቂቅ ሰነድ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል::
የዕለቱ መርሐ ግብር በብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳትና የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከተከፈተ በኋላ በመምህር ዮናስ ፍቅረ የሀገረ ስብከቱ የሰው ሀብት አስተዳደር ዋና ክፍል ኃላፊ የመርሐ ግብር ትውውቅ ከተደረገ በኋላ ህዳር 27 ቀን 2006 ዓ.ም ከሰዓት በፊት በአቶ ታደሰ አሰፋ በአድባራት እና ገዳማት መዋቅራዊ አደረጃጀት ዙሪያ ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን በረቂቅ ሰነዱ የስልጠና እና የአረጋውያን መመሪያ ማዕከል ፕሮጀክትም ተካትቶአል፡፡
በተሰጠው የረቂቅ ሰነድ ውይይት ዙሪያ ተሳታፊዎቹ ሰፋ ያለ ውይይት አካሂደዋል በተጨማሪም ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳትና የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሚከተለው መመሪያ ተሰጥቶአል፡፡
መምህር ዮናስ ፍቅረ የሀገረ ስብከቱ የሰው ሀብት አስተዳደር ዋና ክፍል ኃላፊ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የቤተ ክርስቲያንን መብት ለማስከበር ሲሉ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ከባድ ፈተና አግኝቶአቸዋል፡፡
ቅዱስነታቸው ሕይወት የሰጣቸው እና ቤተ ክርስቲያኒቱ አሁን ለምንመራበት ቃለ ዓዋዲና ሰበካ ጉባኤ እንዲሁም ሰንበት ት/ቤትን ለማቋቋም ብዙ ይሠሩ እንደነበር ይታወቃል፡፡
ከአርባ ዓመት ያላነሰ ቤተ ክርስቲያናችን የተመራችበት ቃለ ዓዋዲ በቅዱስነታቸው አማካኝነት ሥራ እንዲውል የተደረገ ሲሆን ያን ጊዜ ብዙ አሉባልታ ይነዛ እንደነበር ይታወቃል፡፡
ይህ የመዋቅር ረቂቅ ሰነድ ሁሉም ይመክርበታል የሚስተካከል ካለም ይስተካከላል ረቂቅ ሰነዱ ከቃለ ዓዋዲው፣ከህገ ቤተ ክርስቲያን እና ከህገ መንግሥቱም ጭምር ጋር አብሮ እንዲሄድ ሆኖ ነው የተዘጋጀው ሀሳብ መስጠት መወያየት ተገቢ ነው ከዚህ ውጭ የሆነ ሀሳብ ግን ተገቢ አይደለም፡፡ ተወደደም ተጠላም ያለ ህግ መኖር አንችልም ሠራተኞችን መቆጣጠር የሚቻለው ሕግ በሚያስቀምጠው ነው፡፡ የሕግ ባለቤት የሆነችው ቤተ ክርስቲያናችን ያለህግ መኖር እና መሥራት ስለማይገባት ሊገዛን የሚችል ሕግ ያስፈልገናል በማለት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ ከሰዓት በፊት የነበረው የረቂቅ ሰነድ ስልጠና ተጠናቅቆአል፡፡
በአጠቃላይ ውይይቱ ከሰዓት በፊትም ሆነ ከሰዓት በኋላ ከተጠበቀው በላይ አስተማሪና ገንቢ የሆኑ ሃሳቦችን በመሠጠት መግባባትና የቤተ ክርስቲያን ልጅነት በሞላበት መንፈስ በመካሄድ ላይ ሲሆን ለአቅረቢዎቸቱም ጥሩ የሆነ ምስጋና እተቸራቸው ይገኛል፡፡በውጭ የሚነገረውና በተግባር ላይ ያለው ሆኔታ ፈፅሞ የማይገናኙ መሆነቸውን ለማወቅና ለመገንዘብ ተችሏል፡፡በመሆኑም ሁሉም አገልጋዮች ለዚሁ በአይነቱ ልዩ በሆነው መዋቅራዊና አደረጃጀት ረቂቅ ሰነድ ላይ በቀና መንፈስ በገንዘብ የለወጡ ባለቤት እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል፡፡
{flike}{plusone}