በቦሌ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክረስቲያን ይልማት እንቅስቃሴ እየተድረገ መሆኑ ተገለፀ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
በአዲሱ ስም ትጠሪያለሽ ት/ኢሳ 62፣2
ነበየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳያስ ስለ ፅዮን ወይም ስለ እየሩሳሌም መታደስ ስለሚመጣው ብርሃኗና የህይዎቷ ፋናዋ አስቀድሞ በትንቢት ሲናገር‹‹ ስለ ፅዮን ዝም አልልም ስለ እየሩሳሌ ምን ፀጥ አልልም ጽድቋ እንደጸዳል መዳኗም እንደሚበራ ፋና እስኪ ወጣ ድረስ ለህዝቡ ጽድቅሽን ነገስታትም ሁሉ ክብርንሽን ያያሉ……በአዲሱ ስም ትጠሪያለሽ በማለት በተነበየው ትንቢት መሰረት ትንቢቱ የተነገረላት አገረ እግዚአብሔር እየሩሳሌም የመከራ ዘመኗ አለፎ በአዲሱ ስሟ ለመጠራት በተስፋ ብዙ ዘመናት አስቆጥራለች፡፡ እንደዚሁም በምስራቅ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከሚገኙት አድባራት መካከል ይዞታዋ የቦታ ስፋት የምትታወቀው የእኛም የቦሌ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክረስቲያን 1969 ዓ.ም ጀምሮ የተመሰረተ ሲሆን በሰፊው ይዞታዋ ላይ የልማት ስራ ሳትሰራ ለዘመናት ቆይታለች በዚህም ምክንያት ይዞታዋ ጫካ ሆኖ አላፊው አግዳሚውም ቆሻሻሲጥልበት አገልጋይ ካህናቶችን የአጥቢያው በምዕምናን ለመንፈሳዊ አገልግሎትና ከፈጣሪያቸው ጋር በጸሎት ለመገናኘት ሲመጡ ያልታወቁ ወንበዴዎች ጫካውን ከለላ አርገው ወይም ተገን አርገው ለክፉ አደጋ ሲያገለጡ የተመለከቱ አባቶች የእግዚአብሔር ፍቃድ ሲሆን በአዲሱ ስምሽ ትጠሪያለሽ ሳይሉ አላለፉም ስለዚህም የእግዚአብሔር ፍቃድ ሲሆን ድንቅ ስራውን ይሰራ ዘንድ ታላቁና ብልህ አስተዋዩም መሪ ወይም አስተዳደር ታህሳስ 1 ቀን 2004 ዓ.ም ወደ ቤተክርስቲያናችን በሀገረ ስብከቱ መልካም ፍቃድ ተመድበው በተቀደሰው ቤተ ክርስቲያናችን አውደ ምህረት ቆም አሉና እግዚአብሔርን ካመሰገኑ በኃላ ከተቀደሰው ህዝብ ክርስቲያን ጋር በእግዚአብሔር ሰላምታ ተዋወቁ ታላቁ እና እንደበተ ርቱዕ የሆኑት የደብራችን ዋና ጸሓፊ የአርምሞ ጊዜ ተጠናቋልና ከጠቅላይ ቤተ ክህነት የተላከውን ደብዳቤ በልዩ ልዩ የክብር እንግዳዎች እና ሊቃውንት መካከል በተዋበ የአነጋገር ስልታቸው የደብዳቤውን ፅንስ ኀሳብ አስሙ የተጣለባቸውን ኃላፊነትም ከመጡልን አባት ጋራ እጅና ጓንት ሆነው እንደሚወጡ ቃሌ ነው፡፡ በማለት ንግግራቸውን ካከናወኑ በኃላ የገቡትን ኪዳን በተግባር ያሳዩት ውድ እና ብርቅዬው አስተዳዳሪያችን ከደብሩ ሰበካ ጉባኤና የአስተዳደር ሰራተኞች ጋር ከማህበር ካህናቱና ከአጥቢያው ምዕምናን ጋር የስብከት ወንጌል አገልግሎትን በማስፋፋት የሰንበት ትምህርቱን በማጠናከር ቤተ ክርስቲያናችን የልማታ አንበሳደር እንድትሆን ቃል እገባለሁ አሉ፡፡ በጌጠኛ በትህ ልማትይሁን እንዳለ ህዝቡም በእልልታ ተቀበላቸው ይሁን እንጂ ይህ አባባል የተለመደ ነው፡፡ በማለት ተስፋ የቆረጥን በጊዜው ባንኖር አንቀርም የቃል ኪዳኑ ተስፋ ግን እያለመለመ መጣ እና ልማት አንድ ተባለ ልማት አንድ ታዲያ የመጀመሪያው እና አንገብጋቢው የይዞታ ማረጋገጫን ማግኘት ነበር፡፡ ይህን የይዞታ ማረጋጋጫ ለማግኘት ከዚህ በፊት የነበሩት አስተዳደሪዎች ሳይሞክሩት አልቀሩም፡፡
ይሁን እንጂ ጊዜውን ገና ስለነበር አልተሳካም ነበር አስተውሎ የተራመደ ብዙ ርቀት ይጓዛል እንደተባለው ሁሉ ለብዙ ዘመናት በመጓተት የቆየውን የይዞታ ማረጋገጫ ለመያዝ አስተውሎ መራመድ ያስፈልግ ነበር፡፡ አስተዋዩና ብልሁ አስተዳዳሪያችን ከአስተዳደር ስራተኞቻቸውና ከሰበካ ጉባኤ አባላትጋር ጉዳዩን ከጤኑ በኋላ ከቀበሌ ከወረዳ ወደ ከፍል ከተማ ከክፍለ ከተማው ቤተክረስቲያኑ ወደ ማዘጋጃ ጉዞ ማድረጉን ጀመሩ፡፡ ምስጋና ሳይቸራቸው የማይታለፉት የቀበሌ ወረዳ የክፍለ ከተማ ኃላፊዎችም የለመደውንተስፋ ስለ ሰጡአቸው የሚቀጥሉ ስራዎች ተሰሩ፡፡
1. የመጀመሪያው ልማታ ሰላምን ማሰፈን ነበረና የነበሩትን ችግሮች አሰውግድው ሰላምን አሰፈኑ፡፡
2. የይዞታ ማረጋገጫ በእጃች ገባ ኃላፊው አግዳሚው ቆሻሻ መጣያ ያደረገውን የቤተክርስቲያኗ ይዞታ በአውደ ምህረት የትብብር ጥሪ በማስተላላፍ የአጥቢያው ምዕመና ባመጣው ቆርቆር እንዲታጠር ተደረገ፡፡
3. በነበረው ጭቃ ምክንያት ምዕምናን ከቤተክርስቲያ እንዳይርቁ ከወረዳውና ከክፍለ ከተማው ከደብሩ ልማት ኮሚቴ ጋር በመነጋገር (ከመቶ አርባ ሺብር) በላይ ከቤተክርስቲያኗ ካዝና ውጭ ተደርጎ መንገዱ በኮብል እስቶን ተሰራ፡፡
4. የይዞታ መረጋገጫ ወደ እጅ ማስገባት ነበር በዚህ ጊዜ ግን ከአራቱም አቅጣጫ ከባድ ፈታናዎች ነበሩ፡፡ በዚህ ጊዜ ግን አንዳንድ ግለሰቦታ የራሳቸውን ጥቅም የካሄዱበት ነበርና አልተሳካላቸውም ውስጥ ለውስጥ ቤተክርስቲየኒቷን ለመጉዳት ሳይሞክሩ አልቀሩም፡፡ቢሆንም ግን ያለእግዚአብሔርን ፍቃድ መከላከል አይቻልምና ማረጋገጫችን ወደ እጃችን ገባ፡፡የጠ/ቤ/ክ እና ሀ/ስብከቱ የወረዳ ሰራተኞች ጥር 17/2005 ዓ.ም በእጃችን ገባ፡፡
ከተራ ቁጥር 1-4 በጠቀስናቸው የሥራ ውጤቶች መሰረት ማህበረ ካህናቱና የደብሩ ልዩ ልዩ ሠራተኞች የተሰማቸውን ልባዊ ሀሴት ወይም ደስታ ለመግለጽ ከመካከላቸው የሽልማት ኮሜቴ በሟቋቋም-
1.ኛ ሊደብሩ አስተዳዳሪ
2ኛ ለሰበካ ጉባኤው አባልነትና
3ኛ ለደብሩ የአስተዳደር ሰራተኞች
በአካባቢያችን ከሚገኙ የቤተ ክርስቲያኖችን ልማት ከሰጠታቸው ምዕምናን ጋር በመተባበር ይህን የደስታ መግለጫ ሽልማት አበርክተዋል፡፡
4ኛ የይዞታ ማረጋገጫ ቢያዝም ይህ ብቻውን ልማት ሊሆን ስለ ማይቻል የገንባታ ፈቃድ መጠየቅ ግዴታ ነበር፡፡ የቤተክርስቲያናቸን ይዞታ ሰፊ ከመሆኑ አንደፃር ወረዳ እና ለከተማ ብቻ ለማቅ ስለማይቻል ወደ ማዘጋጃቤት ወጣ ማለቱ የግድ ስለነበር ታታሪውን ትጉህ አስተዳዳሪያችን ህልማቸውን እውን ያደርጉ ዘንድ ደከመኝ፣ ስለቼኝ፣ ሳይሉን ርዕቱ በሆነው እና በተዋበው ጠይቀውም በማያፍሩበት” አንደበታቸው ጥያቄ ለማቅረብ ወደ ማዘጋጃ የስተዳደር ሰራተኞች አመሩ፡፡
ከተማው የአስተዳደር ሰራተኞችም ልማቱ እንዲፋጠን ጉጉታቸውና ናፍቆታቸው ነበርና የግንባታውን ፍቃድ ተረከቡ፡፡ በቅጥር ግቢያችን ውስጥ የሚታዩት በርካታ ስራዎች በሙሉ ተሰሩ ቤተክረስቲያችንም የጎጊስጫካና የቆሼ መጣያ የሚባለው ስሟ ተቃይሮ ለልማት ቦታ በሚባለው በአዲሱ ስሟ ተጠራች፡፡
የእግዚአብሔር ስም ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን
አዘጋጅ
የልማትና የሽልማት ኮሚቴው
ለበለጠ መረጃ፡-
09 11 60 44 32
09 11 19 53 86
{flike}{plusone}