በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የሚመራው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለዋና ሥራ አስኪያጅነት እና ዋና ጸሐፊነት ውድድር አካሄደ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እንደ ሌሎቹ አህጉረ ስብከቶች ሁሉ ራሱን ችሎ በሊቀ ጳጳስ እንዲመራ በቅዱስ ሲኖዶስ መወሰኑን ተከትሎ፣ ጽ/ቤቱ ለሚፈልገው ሁለት የሥራ ኃላፊነት መደቦች ማለትም ለዋና ሥራ አስኪያጅነት እና ዋና ጸሐፊነት በውድድር ለመመደብ ህዳር 16 ቀን 2013 ዓ/ም ሀገረ ስብከቱ ባወጣው የውድድር ማስታወቂያ መሠረት ዛሬ ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ/ም ውድድር አካሂዷል ፡፡

በአስተዳደር፡ በፋይናንስ እና በሥነ መለኮት የትምርህርት ዘርፎች የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በመንፈሳዊ የአብነት ትምህርት ደግሞ የአንዱን ምስክርነት የትምህርት ዝግጅት የሚጠይቀውንና በሀገረ ስብከቱ ሥር ባሉት መዋቅሮች በሰው ኃይል እና ፋይናንስ አስተዳደር ቢያንስ 5 ዓመት የሥራ ልምድ በሚያስፈልገው የሥራ መደብ ኃላፊነት ለመወዳደር ስድሳ አራት (64)ተወዳዳሪዎች /አመልካቾች/ ያላቸውን የትምህርት ዝግጅት፡ የሥራ ልምድ እና ሥልጣነ ክህነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ እንዲሁም የአመራር ሐሳባቸውን የሚገልፅ አጭር ንድፈ ሐሳብ በማስረጃነት አቅርበዋል::

የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ያወጣውን ሁለት የሥራ ኃላፊነት መደቦች የውድድር ማስታወቂያ መሠረት በማድረግ የቅጥር ሕጉን በጠበቀ መልኩ አራት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፡ ከተለያዩ የቤተ-ክርስቲያኒቱ ተቋማት እና ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የተውጣጡና አሥር አባላት ያሉት አንድ የባለሙያዎች የቅጥር ኮሚቴ በማዋቀር በተወዳዳሪዎች የቀረቡለትን የተለያዩ ማስረጃዎችን ተመልክቶና ገምግሞ በውድድር ማስታወቂያው ላይ የተቀመጡትን ልዩ ልዩ መሥፈርቶች መመዘኛ በማድረግ ሦስት ዙር የማጣራት ሥራ አድርጓል::

በመጀመሪያው ዙር የማጣራት ሥራ የተዘረዘሩትን መሥፈርቶች ያላሟሉትን አሥራ ስምንት (18) ተወዳዳሪዎችንና በሁለተኛው ዙር የማጣራት ሥራ ከፊል መሥፈርት ያሟሉትን ሰላሳ ሁለት (32) ተወዳዳሪዎችን በጥቅሉ የቅጥር ኮሚቴው በሁለት ዙር የዶክመንት ማጣራት ሥራው ሃምሳ (50) ተወዳዳሪዎችን ከውድድሩ በማግለል ሙሉ መሥፈርቱን ያሟሉት አሥራ አራት (14) ተወዳዳሪዎች ወደ ሦስተኛው ዙር በማሳለፍ ለፅሁፍ እና ለቃል ፈተና እንዲቀመጡ ማድረጉም ተገልጿል::

በመጨረሻም ለፅሁፍ ፈተና ከተቀመጡት አሥራ አራት (14) ተወዳዳሪዎች መካከል አሥሩ (10) ተወዳዳሪዎች ለቃል ፈተና የተቀመጡ መሆናቸውን ከሀገረ-ስብከቱ ሕዝብ ግንኙት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል የመጨረሻ ውጤቱ እንደደረሰን አሸናፊዎቹን ተወዳዳሪዎች የምንገልፅ መሆኑን እናሳውቃለን::

መ/ር ሽፈራው እንደሻው የሀገረ ስብከቱ ዘጋ