በቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ የተላለፈውን ውሳኔ በደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤ/ ክ/ተፈፃሚ መሆን ጀምሯል

መጋቢት 24/2012 ዓ.ም ከቀኑ አስራ አንድ ሰዓት ላይ ክብር የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ አባ ኃይለ ገብርኤል ነጋሽ (ቆሞስ) በደብረ አሚን አቡነ ተከለ ሃይማኖት ገዳም ድንገተኛ ምልከታ አድርገዋል።

በገዳሙ ምንም አይነት የሰርክ ጉባኤ አለመኖሩን የሚገልጽ ማስታወቂያ በደብሩ የስራ ኃላፊዎች ተጽፎ በገዳሙ መግቢያ በር ላይ ተለጥፏል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ትዕዛዝ አክብሮ ማስከበር ከሁሉም የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች፣ ካህናትና ምዕመናን የሚጠበቅ ተግባር ቢሆንም የደብረ አሚን አቡነ ተከለ ሃይማኖት ገዳም የስራ ኃላፊዎች ሊመሰገኑ ይገባል፤ በተለይም የገዳሙ ዋና ፀሐፊ ሊቀ ስዩማን ቀሲስ ጥሩነ ሸዋዬ አርአያነት ያለው ተግባር በመሆኑ ሊመሰገን ይገባዋል።

                               ዘገባው ምንጭ የሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግኑኝነት ዋና ክፍል ነው