በቀራንዮ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በጊዜያዊነት ያረፉት የወይብላ ቅድስት ማርያምና ታቦተ ሚካኤል ወደ መንበረ ክብራቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ!!!
በመንግሥት የጸጥታ አካላትና በወጣቶች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት የተነሣ ወደ ኋላ ተመልሰው ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በጊዜያዊነት ያረፉት የወይብላ ቅድስት ማርያምና ታቦተ ቅዱስ ሚካኤል ወደ መንበራቸው ክብራቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ።
የአዲስ አበባ እና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የተፈጠረውን ችግር በማረጋጋትና ምእመናንንም በማጽናናት ታቦታቱን ወደ መንበረ ክብራቸው የመመለስ ጉዞውን እየመሩ ይገኛሉ።
የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ጉባኤ ቆሞስ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ: የሀገረ ስብከቱና የክፍለ ከተማው የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም እጅግ በርካታ ኦርቶዶክሳዊ ምእመናን በቦታው ተገኝተዋል።
የተፈጠረውን አለመግባባት ምክንያትና በክስተቱ የደረሰውን አጠቃላይ ጉዳት አስመልክቶ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና ሌሎች የቤተ ክርስቲያናችን ክፍሎች የሚሰጡትን ዝርዝር መረጃ ተከታትለን ከቆይታ በኋላ የምናቀርብ ይሆናል።
በመ/ር ሽፈራው እንደሻው