በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መሠረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ሥልጠና ተጀመረ

0020
የካቴድራሉ ሠራተኞች ሥልጠናውን ሲከታተሉ

በሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በካቴድራሉ አስተዳደር አማካኝነት መሠረታዊ የኮምፒውተር ትምህርት /ሥልጠና በካቴድራሉ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለካቴድራሉ ጽ/ቤት ሠራተኞች እና ለተወሰኑ ማህበረ ካህናት ከመጋቢት 20/07/2005 ዓ.ም ጀምሮ ሥልጠናው በመካሄድ ላይ ነው፡፡

የሥልጠናው ዋና አስተባባሪ መ/ር ዘሩ ብርሃኔ እንደተናገሩት፤ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርት ማስተማር ዘመኑን የዋጀ መንፈሳዊና መኅበራዊ አገልግሎት መስጠት ያስችላል በመሆኑም ትምህርቱን እየተከታተሉ ያሉ የከቴድራሉ ሠራተኞች በኮምፒውተር ትምህርት መሠልጠናቸው የመረጃ ሥርዓትና ተዛማጅ ሥራዎች በዘመናዊ መልክ ለማከናወን እንደሚያግዛቸውም ተናግረዋል፡፡

የካቴድራሉ ጽ/ቤት ሥልጠናውን አዘጋጅቶ የካቴድራሉ አባቶች ካህናትና የጽ/ቤት ሠራተኞች በአንድነት እንዲሠለጥኑ ማድረጉ ቤተ ክርስቲያንን በልማት ለማሳደግ ያለውን ርእይ እንደሚያሳይ ጠቁመው፤ ወደፊትም የተለያዩ ሲስተሞችን ለምሳሌ

  • የሰበካ ጉባኤ አባላት መመዝገቢያ ሶፍት ዌር፣
  • የመዝገብ ቤት ፋይል መያዣ ዳታ ቤዝ ሶፍት ዌር፣
  • ኤች አር ሲስተም/HRS/፣
  • እስታስቲካዊ የሆኑ የጋብቻ፣
  • የልደት እና የመሳሰሉ ሲስተሞችን አዘጋጅቶ ሠራተኞች በቀላሉ መደበኛ ሥራቸውን በፍጥነትና በጥራት ማከናወን እንዲቺሉ በባለሞያዎች ሥልጠና ሊሰጥ እንደሚቺል ተናግረዋል ፡፡

የመጀመሪያውን ዙር መሠረታዊ የኮምፒዩተር ሥልጠና እየተከታተሉት ያለው ሥልጠና/ የትምህርት ዓይነት

  • አጠቃላይ ስለ ኮምፒዩተር መግቢያ /Introduction to computer/IT
  • ኤም ኤስ ዊንዶውስ (Ms-wodows /Window XP /7)
  • ማክሮሶፍት ወርድ 2007/10/ Micro soft office word 2007/10
  • ማይክሮሶፍት ኤክሲኤል 2007/10/ Micro soft office excel 2007/10
  • ማይክሮሶፍት አክሰስ 2007/10/ Micro soft office access 2007/10
  • ማይክሮሶፍት ፓወር ፖይንት 2007/10/ Micro soft office PowerPoint 2007/10
  • ማይክሮሶፍት ፐብሊሸር 2007/10/ Micro soft office publisher 2007/10
  • የኢንተርኔት አጠቃቀምና አጠቃላይ ቴክኖሎጀው ለቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊና መኅበራዊ አገልግሎት ያለው ጠቀሜታ የተመለከተ መሆኑን አስተባባሪ ጠቁሞው፣ ሥልጠናው ሠራተኞች አገልግሎታቸውን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለመሥራት እንደሚረዳ እና በአጣቃላይ ዘመኑ/ትክኖሎጂው የደረሰበትን ደረጃ እና የአሰራር ሄደት ለሠራተኞች በወቅቱና በሰዓቱ ማስተዋወቁ ተገቢ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ሥልጠናውን ለ2 ወራት ያህል እየሰጡ ያሉት አሠልጣኞች በአሁኑ ጊዜ በኮምፒዩተር ሳይንስ/በአይቲ ሙያ በተለያዩ ተቋማት የሚያስተምሩ/የሚሠሩ አባላት እንደሆኑ አስተባባሪው አስረድቷል፡፡ ለወደፊትም ሥልጠናውን ከካቴድራሉ በተጨማሪ ወደ ሌሎች መሰል አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት እና መሥራቤቶች በመሔድ ለሚመለከታቸው ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሠረተኞች ይህን የመሰል ሥልጠና መስጠቱ ተገቢ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የኮምፒዩተር ሥልጠናው ካለቀ በኋላም በሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ሲፈቀድ ሌሎች ሥልጠናዎች ማለትም የአስተዳደር እና የሒሳብ አያያዝ ሥልጠናዎች በካቴድራሉ ሊሰጡ እንደሚቺሉ ጠቁመዋል፡፡

የካቴድራሉ አስተዳደር ቀደም ሲል ከ2 ዓመት በፊት ዘመናዊ ድረ ገጽ/ዌብ ሳይት ያሰራ ሲሆን ከ3 ዓመት በፊት በ2ኛ ደረጃ ት/ቤት አገልግሎት በመስጠት ላይ ያለው የብሮድ ባንድ ኢንተርኔት ከካቴድራሉ ጋር ከ500 ሜትር በላይ የሆነውን ርቀት በኔትዎረክ በማገኛት በአሁኑ ሰዓት የካቴድራሉ ጽ/ቤት ሙሉ በሙሉ የብሮድ ብንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ለሠራተኞች መስጠት መጀመሩ አስተዳደሩን እጅግ የሚያስመሰገን የሥራ ውጤት ነው፡፡

ይህም ካቴድራሉን ጨምሮ የካቴድራሉን ሙዝዬም፤የካቴድራሉ ዘመናዊ ት/ቤት በማስተዋወቅ እና ካቴድራሉ በልማቱ በኩል ለሚያደርው እንቀስቃሴ በመላው ዓለም ላይ ከሚገኙ የዕምነቱ ተከታዮች ምዕመናን ጋር እንደ አንድ ሚዲያ ሆኖ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነው፡፡ በመሆኑም ይህ ቴክኖሎጂ የካቴድራሉ አስተዳደር በቀላሉ ት/ቤቱን ለመቆጣጠር፤መረጃን በቀላሉ ለመለዋጥ እና ፕሪንተርና የመሳሰሉትን ሼር ለመድረግ እንዲሁም የሠረተኛውን አቅም በመገንበታ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡

በሌላ ዜና የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን መጋቢት 18 እና 19 ቀን 2005 ዓ.ም በጊዮን ሆቴል ለ318 በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሥር ለሚሠሩ ሰባኪያነ ወንግል በሙስና ዙሪያ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና ሰባኪያነ ወንጌሉ ሙስናን በመከላከል ረገድ በሕብረተ ሰቡ ውስጥ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ የ2 ቀን ሙሉ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡