ሦስቱ መንፈሳውያን ኮሌጆች ያስተማሩአቸው ደቀመዛሙርት በሰርተፍኬት ፣ በዲፕሎማ ፣ በድግሪና በማስተርስ መርሐ ግብር አስመረቁ

g0352
ቅዱስነታቸው ተመራቂዎችን ሲሸልሙ

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ያስተማራቸውን ደቀ መዛሙር በቀን በዲፕሎማ መርሐ ግብር  በማታ በዲፕሎማ መርሐ ግብር በድግሪ መርሐ ግብር በማስተርስ መርሐ ግብር በድምሩ ደቀመዛሙርት ሰኔ 20 ቀን 2007 ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና በርካታ የተመረቁ ቤተሰቦች በተገኙበት ያስመረቀ ሲሆን በዚሁ ዕለት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የምረቃውን መርሐ ግብር አስመልክተው ባስተላለፉት አባታዊ መልእክት
በማለት ሰፋ ያለ አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
በተመሳሳይ የሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሰኔ 25 ቀን 2007 ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ ፖትርያርኩ ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና በርካታ የተመረቁ ቤተሰቦች በተገኙበት በቀን በዲፕሎማ መርሐ ግብር 21 በማታው በዲፕሎማ መርሐ ግብር 181 በትርጓሜ መጻሕፍት ብሉያት /የሐዲሳት 16 በድምሩ 219  ደቀመዛሙርት አስመርቋል፡፡
 እንዲሁም የመቐሌ ከሣቴ ብርሃን ቅዱስ ፍሬምናጦስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በ2007 ዓ.ም በማስተርስ ድግሪ 20 በዲፕሎማ 15 በብሉይ ኪዳን ትርጓሜ 12 በአድቫንስ ስታንድ ድግሪ 6 በኤክስቴንሽን 45 በርቀት 96 በሠርተፍኬት 96 ተቀብሎ በማስተማር ላይ የሚገኝ ሲሆን በያዝነው ዓመት ትምህርታቸውን አጠናቅቀው ለምረቃ የበቁት ደቀ መዛሙርት 126 ናቸው፡፡ ስለሆነም ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የመቐሌ ከተማ ዞን መስተዳድር ተወካይ ፣ የመቐሌ ዩኒቨርሲቲ ተወካይ ፣ የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፣ የመቐሌ ሀገረ ስብከት ተወካዮች በተገኙበት ሰኔ 27 ቀን 2007 ዓ.ም በሰርተፍኬት 96 በዲፕሎማ መርሐ ግብር 18 በድግሪ መርሐ ግብር 12 በድምሩ 126 ደቀመዛሙርትን አስመርቋል፡፡ በመርሐ ግብሩ በዓል ወቅት በከፍተኛ የቅኔ ባለሙያዎችና መምህራን የተለያዩ ቅኔያት ቀርበዋል፡፡ ከቀረቡት ቅኔያት መካከል በመምህር ያሬድና በአባ መልአኩ የቀረቡትን ቅኔያት እንደሚከተለው አቅርበናቸዋል፡፡
በመምህር ያሬድ መወድስ
ግረምተ ባህርይ ኦፍ ቤተ ክርስቲያን 
-ዘተዋሕዶ ወለደት ማትያስሃ ዕንቆ ባህርይ፣
-እንበለ ሩካቤ ጉህሉት ወእንበለ ዘርዕ እከይ
-እምዘ በኦ ውስተ ከርሣ ሥርአት ፀዳለ ዘሀሎ ሲኖዶስ ፀሐይ፣
-ወእንዘ ንበረታ ውስተ ቀላይ፣
-ኢትዮጵያ ተረክቦ በኢትዮጵያ ቀላይ፣
-ይትፌኖሂ ኃበ ዓለም እምአፈ ሊቃውንት ሰማይ፣
-ዘነቢያተ ፅዮንሰበክዎ ትምህርተ ወንጌል አዶናይ፣
-ይቤ ገሀደ ቃለ ማትያስ ነቢይ፣
-አኩኑ አዘከርዎ ትንበት ወራዕይ
በአባ መልአኩ ታከለ ሥላሴ ቅኔ
እፈቅድ ወእትመነይ፣
ሀበ ተአዛዚ ዘወልደ አብ
ዘርእዘ ከሰተ በሀቦ ሲና ዘሴሎ
-በመልአክ ዘፊልድልፊያ ማትያስ ይምሰሎ፣
-መራሁተ ዳዊት ዐቢይ እስመ በሀቤከ ሀሎ፣
-ወአስተጋብአ በተልዕሎ፣
-ተጋድሎ ሥጋ ቅድስተ ዘተጋድሎ፣
-ዘእግዚእ ዘይእሕዝ ኵሎ፣
በመቀጠልም ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚከተለውን መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ “ህየንተ አበውኩ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ፣ ወትሰይሚዮሙ መላእክተ ለኵሉ ምድር፣ ወይዘክሩ ሰመኪ በኵሉ ትውልደ ትውልድ” ወንጌልን ለዓለም እንዲአደርሱ ባባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ፡፡
ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ከዳዊት መዝሙር የተገኘ ሲሆን ለቤተ ክርስቲያንም ሆነ ለሀገር ሊጠቀስ ይችላል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለኢትዮጵያ የሰጠው ፀጋ ትልቅ ነው፡፡ በዙሪያችን የምናያቸው አደገኛ አዝማሚያዎች አስፈሪዎች ናቸው፡፡
ስለሆነም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ወንጌልን በምታስተምርበት ጊዜ ስለሀገር ፍቅር ፣ ስለአንድነት ፣ ስልነፃነት ፣ ስለፍትሕ ስለመልካም አስተዳደር ታስተምራለች፡፡ ሀገር ከለማች ስደት የለምና፡፡
ስለዚህ ለልማቱ ሁሉም እንድተባበር ማስተማር ይገባል፡፡ ተመራቂ ደቀ መዛሙርትም በዚህ ዓላማ መሰለፍ አለባቸው አባቶቻችን በነበራቸው ፅኑ እምነትና ሀገር ወዳድነት ሀገራችንን እስከ አሁን ድረስ ጠብቀው አቆይተውልናል፡፡ እኛም በበኩላችን ይህ ቀኖና ፣ይህ ትውፊት፣ ይህ ትምህርት ለትውልድ እንዲአልፍ በርትተን መሥራት አለብን ፤ ይህንን ኃላፊነት መወጣት አለብን ፤ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል “ማዕረሩሰ ብዙህ ወገባሩኒ ህዳጥ አዝመራው ብዙ ነው ሠራተኞቹ ግን ጥቂቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ የአዝመራውን ባለቤት ሠራተኛ እንዲጨምር ለምኑት ይላል፡፡
ጌታ ሐዋርያትን ብቻ መርጦ አላቆመም ፤ የሐዋርያትን ተከታዮች መርጦአል፡፡ አሁንም ቤተ ክርስቲያን በየጊዜው እያስተማረችና እያሰለጠነች ደቀመዛሙርትን ታሠማራለች ፤ በዚሁ መሠረት ነው አሁን ደቀ መዛሙርትን ያስመረቅነው ፤ በማለት ቅዱስነታቸው ሰፊ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

{flike}{plusone}