መጋቤ ሃይማኖት ግርማይ ሐዲስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሒሳብና በጀት ዋና ክፍል ሐላፊ ሆነው ተመደቡ
በመ/ር ሣህሉ አድማሱ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ዋና ሒሳብ ሹም ሆነው ሲሠሩ የቆዩት መጋቤ ሃይማኖት ግርማይ ሐዲስ በቁጥር 1984/0829//2011 በቀን 17/04/2011 ዓ.ም ከሀገረ ስብከቱ በተጻፈ ደብዳቤ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ሀገረ ስብከት በሆነው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሒሳብና በጀት ዋና ክፍል ሐላፊነት ተመድበዋል፡፡
መጋቤ ሃይማኖት ግርማይ ሐዲስ በተለያዩ የቤተ ክርስቲያናችን የሥራ መስኮች በመንበረ ፖ/ቅ/ቅ/ማርያም፤በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ፤በቦሌ ደ/ሳ/መድኃኔዓለምካቴድራልና በላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል አብያተ ክርስቲያናት በኃላፊነት እየተመደቡ ሲሠሩ የቆዩ ሲሆን በሠሩባቸው የሥራ ቦታዎች ሁሉ መልካም ስም እንዳላቸው ብዙዎች ይናገራሉ፡፡
የትምህርት ዝግጅታቸውን በተመለከተ በአካውንቲንግ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ሲሆን በአሁን ሰዓት በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ በነገረ መለኮት በድግሪ መርሐ ግብር ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡
መጋቤ ሃይማኖት ግርማይ ሐዲስ ሙስናን ከሚፀየፉ የቤተ ክርስቲያኒቷ ልጆች መካከል አንዱ ሲሆኑ በቅርብ ጊዜ ከተመደቡ የሀገረ ስብከቱ የሥራ ሐላፊዎች ጋር በመሆን በተለይም የሒሳብ አሠራሩን በአገርኛ(አማርኛ)ቋንቋ በማዘመን ለአሠራር፤ለአጠቃቀምና ለሥልጠና ምቹ የሆነ ሲስተም በማመቻቸት ጥሩ ሥራ እንደሚሠሩ ይጠበቃል፡፡
መጋቤ ሃይማኖት ግርማይ ሐዲስ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው የዝግጅት ክፍላችን ይመኝላቸዋል፡፡