መልካም አስተዳደር በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት

“በተለያዩ ምክንያት ከመደበኛ ሥራቸውና ደመወዛቸው ተፈናቅለው የነበሩና ጉዳያቸው በቅ/ሲኖዶስ ደረጃ ተይዞ አጀንዳና መነጋገሪያ የነበረው የሀገረ ስብከቱን መልካም ስምና በጎ ገጽታ ያጎደፈውና ለተቋማዊ ሥራ ማነቆ ሆኖ የቆየው ይሄው አጀንዳ ነው፡፡
በዚህ የተነሳ ተፈናቃዮች ከአፋቸው ላይ የተነጠቀ እንጀራቸውን ለማስመለስ በጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ በየፍ/ቤቱ በየመንግሥት መ/ቤቶች ፍትሕ እናገኝበታለን ብለው ባመነበት ቦታ ሁሉ ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸው እሙን ነው፡፡
ይህንን መራራና አሰቃቂ ክስተት ለመፍታትና እንባቸውን ለማበስ ከሥራዎች ሁሉ ለቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔና ለተፈናቃዮቹ ቅድሚያ በመስጠት እስከ ምሽቱ 3 እና4 ሰአት ድረስ በማምሸትና የማጣራት ሥራ በመሥራት በመጀመሪያ ዙር 68 ለሦስት ዓመታት የተንከባለለ የይጽደቅልን ጥያቄ 60 እና በሁለተኛ ዙር 97 ተፈናቃይ በድምሩ 157 ተፈናቃይ ሰበር ዜና በሚመስል መልኩ በአንድ ቀን ደብዳቤ በማውጣት የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በብፁዕነታቸው ቆራጥ አመራር ሰጪነት አንድም ሠራተኛ ሳይፈናቀል በጠቅላላው 225 ሠራተኞችን በመመደብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለቅዱስ ሲኖዶስ ለተፈናቃዮችና ቤተሰቦቻቸውን እረፍት በሚሰጥ መልኩ የተፈናቃይን ምዕራፍ ለመዝጋት ተችሏል፡፡ለዚህ ታላቅ ስኬትም አዲስ በጀት ከፍተው ተፈናቀይን ለተቀበሉልን የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፡ ምክትል ሊቃነ መናብርትና ባለድርሻ አካላት ሁሉ በእጅጉ ተመስጋኞች ናቸው”
ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት የተወሰደ