ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሠራተኞች መሰረታዊ የቴክኖሎጂ ሥልጠና መስጠት ተጀመረ

(ነሐሴ 22 ቀን 2013 ዓ/ም)

አዲስ አበባ: ኢትዮጵያ
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የዋና ክፍል፣ የክፍልና ልዬ ልዩ ሠራተኞች በሀገረ ስብከቱ የኮምፒዩተር ማሰልጠኛ ማዕከል መሰረታዊ የቴክኖሎጂ ሥልጠና መውሰድ ጀምረዋል።
ሥልጠናው በብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መልካም ፈቃድ በሀገረ ስብከቱ አይቲና ዶክሜንቴሽን ዋና ክፍል አስተባባሪነት የተዘጋጀ ነው።
ሥልጠናው የሚሰጠው ሥልጠና ለመውሰድ የተዘጋጀውን ቅጽ ለሞሉ 41 ሠራተኞች ነው።
በሥልጠናው የተካተቱ ኮርሶች ማይክሮ ሶፍት ዊንዶውስ 2010፣ ማይክሮ ሶፍት ኦፊስ ዎርድ 2010፣ ማይክሮ ሶፍት ኦፊስ ፓዎር ፖይንት፣ ማይክሮ ሶፍት ኦፊስ ኤክስኤል፣ የማኅበራዊ ሚድያ አጠቃቀም፣ የበይነ- መረብ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ የኢንተርኔትና ኢ-ሜል አጠቃቀም፣ ኔትወርክ ሴኩሪቲ እና ፒችትሪ 2010 መሆናቸውን በአስተባባሪው ተጠቁሟል።
ሥልጠናው የሚሰጡ ባለሙያዎች የሀገረ ስብከቱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አማካሪ ኮሚቴ አባላት ሲሆኑ በየሣምንቱ ቅዳሜ ከ2:30 እስከ 7:00 ሰዓት እየተሰጠ ለ15 ቀናት ያህል ሥልጠናው እንደሚሰጥ ዋና ክፍል ኃላፊው ገልጸዋል።
በዛሬው ዕለት መሰረታዊ የኮሞፒተር ሥልጠና በመ/ር ፀጋው በለጠ እና ኢንጂነር ዳዲ ወይፈን የተሰጠ ሲሆን የዛሬ ሣምንት ነሐሴ ቅዳሜ 29/2013 ዓ.ም ሥልጠናው በዚሁ መልኩ እንደሚቀጥል ከወጣው የሥልጠና መርሀ ግብር መረዳት ተችሏል።


ዘጋቢ መ/ር ኪደ ዜናዊ