የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት “መገናኛ ብዙኃን ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ” በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው የሦስት ቀናት ሥልጠና ተጠናቀቀ።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት “መገናኛ ብዙኃን ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ” በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው የሦስት ቀናት ሥልጠና ተጠናቀቀ።
ሀገረ ስብከቱ Takeoff Digital ከተባለና መቀመጫውን ዱባይ ያደረገ በcyber Security and Artifical Intelligence ከሚሠራ ድርጅት ጋር በመተባበር በማኅበራዊ ትሥሥር ገጾች አጠቃቀም ዙሪያ በተመለከተ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ከሁሉም ገዳማትና አድባራት ለተውጣጡ በርካታ ቁጥር ላላቸው ሠልጣኞት ሥልጠናው ተሰጥቷል።
ሥልጠና በብፁዕነታቸው ቡራኬና አባታዊ መልእክት የተከፈተ ሲሆን ቀጥሎም በተለያዩ አሠልጣኞች በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ገለጻና ተግባራዊ ሥልጠና ተሰጥቷል።
የሥልጠናው ተበባሪ አዘጋጅና የ Takeoff Digital ድርጅት ባለቤትና መሥራች የሆኑት ዲ/ን ሰው መሆን ክንዱ ሥልጠናው ገለጻ ብቻ ሳይሆን ተግባራዊ ልምድ ያቀናጀ በመሆኑ ጥቅሙ በርካታ አገልጋዮችን የበይነ መረብ ሚዲያውን ለተፈለገበት ዓላማ በአግባቡ እንዲጠቀሙበት በር ይከፍታል ብለዋል።
አክለውም ኦርቶዶሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን የሕያውን ወንጌል አደራዋን ለመወጣት ይቻል ዘንድ በዚሁ ዘርፍ የሰለጠኑ በርካታ አገልጋዮች ማፍራት ተገቢ በመሆኑ ከብፁዕነታቸው ጀምሮ ሀገረ ስብከቱ ለዚህ ሥራ ትኩረት በመስጠቱ በእጅጉ አድንቀዋል።
በቀጣይ ተከታታይ ሥልጠናዎች በየደረጃው እንዲሰጥ የሞያ ዐሥራታቸውን ለቤተ ክርስቲያን ለመስጠትና ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ሰልጣኞቹም በበኩላቸው የተሰጠው ስልጠና በእጅጉ ጥሩ እንደነበረ አስታውሰው መርሐ ግብር በመዘጋጀቱ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አክለውም ሥልጠናው ተከታይነት እንዲኖረው የጠየቁ ሲሆን በዚህ ሁሉ መመሪያ ለሰጡ ለብፁዕነታቸው እንዲሁም ለሀገረ ስብከቱ ለሥልጠናው ለሰጡ ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል።
የሦስት ቀናቱን ሥልጠና አጭር ሪፖርት የሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግንኙነት ዋና ክፍል ሐላፊ መጋቤ ሐዲስ ዘለዓለም ምሕረቴ ያቀረቡ ሲሆን ሥልጠናው የቤተ ክርስቲያን ሕያውን ተልእኮ ለማፋጠንና ተቋማዊ መናበብን ለማጠናከር እንደሚረዳ ገልጸዋል።
በዚህም ሥልጠና ትብብር ያደረጉትና የድርሻቸውን የተወጡትን አካላት ያመሰገኑ ሲሆን በተለይም የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራልን አስተዳዳርን በእጅጉ አመስግነዋል።
ዲ/ን ሰው መሆን ክንዱ ከዚህ ቀደም የብፁዕ አቡነ ሄኖክ የሀገረ ስቡከቱ ሊቀ ጳጳስና የተዋሕዶ ሚዲያ ማእከል የፌስቡክ ገጾች በሦስተኛ ወገን ተጠልፈው በነበሩበት ወቅት እንዲመለሱ ያደረገ በዘርፉ ባለሙያ መሆኑ የሚታወስ ነው።
በመጨረሻም በብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የተዋሕዶ ሚዲያ ማእከል የበላይ ጠበቂ ቡራኬና ቃለ በረከት የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።
በመርሐ ግብሩ ከብፁዕነታቸውን ጋር ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ መልአከ ብርሃን ሩፋኤል የማነ ብርሃን የቦሌና ለሚኩራ ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ፣ ሊቀ ኅሩያን ዮሐንስ ቀኖ የብፁዕ ሊቀ ጳጳስ ልዩ ጸሐፊ፣ የሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግነኙነት ዋና ክፍል ሐላፊ መ/ሐዲስ ዘለዓለም ምሕረቴ፣ ሌሎች የሀገረ ስብከቱና የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት የሥራ ሐላፊዎች ተገኝተዋል።
Source:-አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ