የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ባሕረ ጥምቀት ቦታ የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲሰጥ ሥራዎች መጀመራቸው ተገለጸ።

የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ባሕረ ጥምቀት ቦታ የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲሰጥ ሥራዎች መጀመራቸው ተገለጸ።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በቦሌና ለሚኩራ ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሥር የሚገኘው የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል የባሕረ ጥምቀት ከተማ አስተዳዳሩ ከሚከተለው የኮሪደር ልማት ጋር በተገናዘበ መልኩ አገሎግሎት የሚሰጡ የተለያዩ ፕሮጆክቶች እንደሚሠሩበት የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አክኪያጁ መልአከ ብርሃን ሩፋኤል የማነ ብርሃን ገልጸዋል።
ይህንን የሥራ እንቅስቃሴ ጅማሮን አስመልክቶ በቦታው የተገኙት የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ በበኩላቸው የጥምቀት ማክበሪያ ቦታዎችን የቤተ ክርስቲያንን ክብርና መልክ በሚመጠን መልኩ የዘመኑን የዋጁ አገልግቶት ሰጪ ፕሮጆክቶችን መሥራት አስፈላጊነቱ በእጅጉ የጎላ ነው ብለዋል።
አክለውም የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ሰበካ ጉባኤ ከክፍለ ከተማው ቤተ ቤተ ክህነት የቅርብ ክትትል ጋር በመሆን በፍጥነት ሥራዎቹ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተስፋቸውን ገልጸዋል።
ይህ ባሕረ ጥምቀት በከተማው ውስጥ ካሉት ፸፱ የጥቀምቀት ማክበሪያ ቦታዎች በምሳሌነት እንደሚጠቀስ የገለጹት ዋና ሥራ አስኪያጁ ከሀገረ ስብከቱ ጀምሮ የክፍለከተማው ቤተ ክህነት እንዲሁም የአጥቢያው ሰበካ ጉባኤ ማኅበረ ካህናትና ምዕምናን ትብርርብ እንዲያደርጉላቸው አሳስበዋል።
የክፍለ ከተማው ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ሩፋኤል የማነ ብርሃን በበኩላቸው በቤተ ክርስቲያናችን ዘመኑን የዋጀና ለትውልዱ ቅርብ የሆኑ ሥራዎችን መሥራት በሁሉም አቀፍ የአገልግሎት መስክ መስጠት ይኖርብናል ብለዋል።
መንግሥት በሰጠው የጥምቀት ማክበሪያ ቦታ ላይ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመተባበር ቦታው ዓመት ሙሉ ለህዝብ አገልግሎት የሚስጥ የልማት ሥራዎችና ሥርዓተ አምልኮ የሚፈፀምበት የቅዳሴና የጥምቀት አገልግሎት የሚሰጡ ልማቶች እንደሚገነቡበትም አብራርተዋል።
በመጨረሻም በዚህም ባሕረ ጥምቀት ቦታን የማስዋብ የሥራ ጅማሮን የጎበኙትን የሀገረ ስብከቱን ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስን አመስግነዋል።

Source:-አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ