ወላጅ አጥና ለችግር የተገለጡ ህጸናት

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እንደሌሎች ሀገረ ስብከት ሁሉ ከሚሰጠው ልዩ ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎት በተጓዳኝ ለማኅበረ ሰቡ የሚጠቅም ሀሳብ በመቅረፅና ከልዩ ልዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት በመሥራት በከማዋ ለሚገኙ ዜጎች ልዩ ልዩ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

በተለይ ወላጆቻቸውን በሞት ያጡና ለችግር ለተጋለጡ ህጻናት፣ ጧሪ ቀባሪ ላጡ አረጋውያን ከኤች አይ ቪ ጋር የሚኖሩ ወጎኖት ወዘተ ድጋፍ እና እንክብካቤ እንዲሁም ዘለቄታዊ የኑሮ መቋቋሚያ ድጋፍ ከIocc ከግሎባል ፈንድ እና ከመሳሰሉት ለጋስ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ፆታን ፣ ዘር፣ ሃይማኖትን ሳይለይ በርካታ ህብረተሰብን ተጠቃሚ ተደርጓል፣ በመደረግም ላይ ይገኛል፡፡ ከላይ በተጠቀሱትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከግማሽ ያላነሱ የከተማዋ ዜጎች ከኘሮጅክቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተደረገ ይገኛል፡፡

ለዚህም በጤና እና ተያያዥ ጉዳዮች ጉዳት ለደረሰባቸው እና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በመምርያ ደረጃ የምግባረ ሰናይ እና የበጎ አድራጎት ክፍል ከሚያደርጋቸው በርካታ ስራዎች በተጓዳኝ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር የሚንቀሳቀስባቸው ሶስት ትልልቅ ቅ/ጽ/ቤቶችን አቋቁሞ ከልማትና ክርስቲያናዊ ተራድዖ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ሰፊ ሥራ በተደራጀ መልኩ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ፕሮጅክቶች መካል አንዱ የግባል ፈንድ 7ኛ ዙር ፕሮጅክት  ነው፡፡

  • በዚህ ፕሮጅክት ብቻ እ.ኤ.አ ከ2009 ጀምሮ በቀትታ ከፕሮጅክቱ ድጋፍ እና እንክብካቤ የሚደረግላቸው የወላጅ አጥ፣ ለችግር የተጋለቱ ህጻናት ብዛት 1855 ሲሆን ለእነዚህ ተረጂዎች በፕሮጀክቱ የሚፈቀው የገንዘብ መጠን ያለሟቋረጥ በየወሩ ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል፡ ይህም ለምግብ፤ ለመጠለያ፤ ለጤና እና ለመሳሰሉት የሚሆን ሲሆን ትምህርታቸውን በድጋፍ እጦት እንዳያቋርጡ የትምህርት መርጃ መሰሪያ መግዣ የሚሆን ገንዘብም  ይሰጣቸዋል፡፡
  • ከዚሁ ድጋፍ ጎን ለጎን የተረጂነትን መንፈስ ለመቀነስ ሲባል በተለይ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ መንግስት በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ ካስቀመጣቸው መርሆች ጋር በማስማማት ሀገር ስብከቱ እነዚህን ተረጂዎች በጥቃቅንና አንስተኛ በማደራጀትና ለመነሻ የሚሆን ገንዘብ ከሰጠ በኋላ አፈጻጸሙን በየጊዜው ይገመገማል፡፡
  • በዚህም ላለፉት አራት አመታት ከ320 በላይ ዜጎች እንዲደራጅ ተደርጎ በስራ ላይ ተሰማርተዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል አብዛኞቹ ውጤታማ መሆናቸውን ሀገረ ስብከቱ ተገንዝቧል፡፡
  • በሌላ በኩል ወላጆቻቸውን በማጣታቸውና ተጓዳኝ በሆኑ ችግሮች ሳብያ የተስፋ መቁረጥና በመጥፎ ሰነ ምግባር የተጠመዱትን ህጻናት የስነ ልብና ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል፤ በዚህም መሰረት በአማካኝ በዓመት ከ13000 ወላጅ አጥና ለችግር የተጋለቱ ህጻናትና ሞግዚቶቻቸው የድጋፉ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
  • ሀገረ ስብከቱ እንዲህ አይነቱ ድጋፍ በተጠናከረ መልኩ እንዲቀትል ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ስራ አየሰራ ቢሆንም ይህ የተጀመረው ስራ በፕሮጅክቱ መጠናቀቅ ምክንያት ተረጂዎች ወደ ቀደመው እንግልት እንዳይገቡ በ36 አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙ መምህራን ወንጌልን በማሰልጠን ምዕመናንን አስተባብረው ይህንን የተቀደሰ አላማ እንዲደግፉ ለማስተባበር የማህበረሰብ ወይይት /የማህበረሰብ ንቅናቄ/ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡በዚህም በአማካኝ በአንድ ሩብ ዓመት ከ500 በላይ ወላጅ አጥና ለችግር የተጋለጡ ህፃናት ተጠቃሚ እሆኑ የገኛሉ፡፡
  • ከላይ የተዘረዘሩትን የድጋፍ እና እንክብካቤ እንዲሁም የማህበረሰብ ውይይት ለማከናወን ከ50 በላይ አድባራትና ገዳማትን ማዕከል ያደረገ ሲሆን በነዚህም አድባራትና ገዳማት ውስጥ በተቋቋመው ኮሚቴ /ከደብሩ አስተዳደር፣ ከቀበሌ፣ ከምዕመናን፣ ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት/ አማካኝነት ስራው በተቀላጠፈ ሁኔታ እየተተገበረ ይገኛል፡፡ ይህም ሀገረ ስብከቱ ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች በመጡ በጥራትና በቅልጥፍና ፕሮጅክቶችን የመተግበር አቅም እንዳለው ያሳያል፡፡
  • ስለዚህ በመላ ዓለም የምትኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ አባላትና ሌሎች የዚህ የተቀደሰ ዓላማ ያላችሁ ዜጎች ይህንን መልካም ተግባር በገንዘብ እንድትደግፉ እና ከሀገረ ስብከቱ ጋር በመተባበር መሥራት እንደምትችሉና እስከ ታች ድረስ በተዘረጋው መዋቅር ተሰማርታችሁ ታች ላለው ዜጋ መድረስ ማለት ስለሆነ ሀገረ ስብከቱን በማንኛውም ጊዜ መጥታችሁ ማነጋገር የምትችሉ መሆን ይገልጻል፡፡